Addis Zeybe - አዲስ ዘይቤ ری ٹویٹ کیا
Addis Zeybe - አዲስ ዘይቤ
8.5K posts

Addis Zeybe - አዲስ ዘይቤ
@AddisZeybe
Discover #Ethiopia’s exquisite urban culture, History, updated #news, and more.
ኢትዮጵያ شامل ہوئے Mart 2018
38 فالونگ27.4K فالوورز

የመንግሥት ኃይሎች በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙት የጅምላ ግድያና የድሮን ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ሲሉ አምስት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠየቁ
መስከረም 10፤ 2016 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤አዲስ አበባ) አምስት የተፎካካሪ ፓርቲዎች ዛሬ ባወጡት ወቅታዊ መግለጫ በዘመነ ኢሕአዴግ ለተፈጠሩ ስህተቶች ሁሉ ይቅርታ ጠይቆ መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠረው የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ሕዝብ እምነትና ተስፋ አምክኗል ሲሉ አስታወቁ።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ፣ እናት ፓርቲ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በጋራ መግለጫቸው የመንግሥት ኃይሎች በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙት የጅምላ ግድያና የድሮን ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀዋል።
ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው አሁንም ብቸኛዉ መንገድ “ዉይይትና ድርድር” በመሆኑ መንግስት ግንባር ቀደም ኃላፊነቱን በመወጣት የድርድር ጥያቄ እንዲያቀርብ፣ የመንግሥት ኃይሎች ከሰፈሩባቸዉ የመደበኛና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአስቸኳይ እንዲለቁ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አክለውም ባልታወቁ ሥፍራዎች በጅምላ ማጎሪያዎች የታሰሩ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ተዋጊ ኃይሎች ዓለም አቀፍ የጦር ሕጎችንና ይህንኑ የሚደነግገውን የጄኔቫ ስምምነት እንዲጠብቁ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማት ግጭቶች በድርድር እንዲፈቱ ጫና ማድረግ አለባቸው ሲሉ ፓርቲዎቹ በሰጡት መግለጫ አሳስበዋል።
አሁን በስልጣን ላይ ያለው የብልፅግና ፓርቲ የመፍትሔ ሀሳቦች ቸል በማለት ችግሮችን በኃይል አማራጭ ለመፍታት በሚያደርገው ሙከራ በሀገር ላይ ለሚደርሰው የከፋ ጉዳት በታሪክም፣ በሞራልም በሕግም ተጠያቂ ይሆናል ብለዋል። ሙሉ መግለጫው ከታች ተያይዟል።


AM

📻 የጦር እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እንዳይመረመሩ የኢትዮጵያ መንግስት ጫና እያደረገ መሆኑን ተመድ አስታወቀ ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ:👇am.addiszeybe.com/featured/addis…
AM

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ በ'ዘላቂ የልማት ግቦች' ከተያዙ እቅዶች እስካሁን 15 በመቶ የሚሆነው ብቻ መሳካቱን ገልፀው ግጭቶች፣ ረሀብ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎች አሁንም ችላ መባላቸውን አሳስበዋል። ሙሉ ዘጋባውን ያንብቡam.addiszeybe.com/featured/addis…

AM

Exciting News! 🌟 The #Gedeo Cultural Landscape in #Ethiopia 🇪🇹 has earned a well-deserved spot on the prestigious @UNESCO #WorldHeritage List. A momentous recognition of our rich cultural heritage! 👏🌍 #EthiopianHeritage #CulturalLandmark

Ethiopia 🇪🇹 English

📢 Just released! The Ethiopian Human Rights Commission's @EthioHRC annual report sheds light on critical social and economic rights challenges in #Ethiopia. Discover the key findings of the ended Ethiopian year and the call for urgent action. Read the full article here! #HumanRights #EthiopiaReport 🇪🇹
addiszeybe.com/addis-ababa/ne…

English

🚫 አጎአን ጨምሮ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለአንድ ዓመት አራዘመ።
የአሜሪካ መንግስት በትግራዩ ጦርነት ሳቢያ በኢትዮጵያ የጣለችው ማዕቀብ አሁንም አሳሳቢ የደህንነት ሁኔታዎች በመኖራቸው ለቀጣይ አንድ ዓመት እንዲራዘም ፕሬዝዳንት ባይደን ወሰኑ።
የአዲስ ዘይቤ ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ am.addiszeybe.com/addis-ababa/Th…

AM

በመቀሌ የተቃውሞ ሰልፍ ከ120 በላይ ሰዎች ሲታሰሩ በርካቶች በፖሊስ እንደተደበድቡ እና የታሰሩት የሶስቱ ፓርቲዎች ሊቃነመናብርት ካደሩብት ተወስደው የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል።
የአዲስ ዘይቤ ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ am.addiszeybe.com/featured/addis…...

AM

Exciting news: An Ethiopian-born cognitive scientist, Abeba Birhane, @Abebab is being recognized as one of TIME's 100 most influential individuals in artificial intelligence for her groundbreaking work in auditing datasets. Her efforts are bringing much-needed transparency and accountability to the industry. #AI


English

የሐረሪ ክልል ፖሊስ በከተማው የደረሰውን የእሳት አደጋ መነሻና ኪሳራ እያጣራሁ ነው አለ
ጳጉሜን 2፤ 2015 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) በሐረሪ ክልል በተለምዶ ሸዋበር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ለጳግሜ 2 ቀን 2015 ዓ.ም አጥቢያ ከለሊቱ 10:00 ሰአት ገደማ ሸዋበር የሸቀጣሸቀጥ መደብር በተባለ ስፍራ እስካሁን "ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ" የእሳት አደጋ ደርሷል።
አደጋው ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይዛመት መደረግ ተችሏል ያለው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን "ከአደጋው ጋር በተገናኘ መንስኤውን እና የወደመውን ንብረት ግምት" ፖሊስ እያጣራ ይገኛል ብሏል። የምርመራው ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

AM

የዓረና ፓርቲ ሊቀ መንበር ዓምዶም ገብረስላሴን ጨምሮ ዛሬ ብቻ ከ20 በላይ ሰዎች ታሰሩ
ጳጉሜን 2፤ 2015 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) በትግራይ ክልል 'ጥምረት ለስር ነቀል ለውጥ” በሚል የተሰባሰቡ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬ እለት ከጠሩት ሠላማዊ ሰልፍ ጋር ተያይዞ ከጠዋት ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከወጣበት ሰዓት ድረስ ቢያንስ ከ20 የሚበልጡ ሰዎች ታስረዋል ተባለ።
የሠልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል እና የውድብ ናፃነት ትግራይ (ውናት) ምክትል ሊቀ መንበር አለምሰገድ አረጋይ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት “ሰልፉን የሚያስተባብሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎቹ የተውጣጡ የኮሚቴ አባላቶች በሙሉ ከሁለት አስተባባሪዎች በስተቀር ታስረዋል”።
እንደ መረጃ ምንጮቹ ከሆነ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ብቻ ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራርና አባላት ብቻ ዓምዶምን ጨምሮ 13 ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፣ ስድስት የቀድሞ የትግራይ ሠራዊት (ቲዲኤፍ) ሰዎች፣ አራት ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ንፁሃን ሰዎች በአጠቃላይ ከ20 በላይ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል።
ሰላማዊ ሰልፉ የተጠራበት ሮማናት አደባባይ አካባቢ “ከሰልፈኞች ቁጥር ያለተናነሰ የፀጥታ ኃይል” መኖሩ የተገለፀ ሲሆን አሁንም በሰልፈኞች እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ግብግቡ እንደቀጠለም ተገልጿል።

AM

Opposition Parties' Officials and Supporters Arrested Amid #Tigray Interim Administration Protest | article – Addis Zeybe addiszeybe.com/featured/addis…
Ethiopia 🇪🇹 English

#updates
የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮቹ በድጋሜ ታስረው ወደ ቀዳማይ ወያነ ማረሚያ ቤት ተወሰዱ
በትግራይ ክልል ከነገ ጀምሮ በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሳቢያ ዛሬ ረፋድ ላይ ታስረው ከሰዓታት እስር በኋላ የተፈቱት የሳልሳይ ወያነ ሊቀ መንበር ሃያሉ ጎዲፋይ፣ የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀ መንበር ዶ/ር ደጀን በርሀ እንዲሁም የባይቶና ዓባይ ትግራይ አመራር አቶ ክብሮም በርሀ በድጋሜ መታሰራቸውን የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ገለፁ።
AM




