
እነኳን ለ2018 ዓ.ም አደረሳችሁ!
**************
*የአማራ ህዝብ ዋስትና ለሆንከው ለመላው የአማራ ፋኖ!
*በየ እስር ቤቱ ታጉራችሁ በስቃይ ለምትገኙ የአማራ ልጆች!
*ለአማራ ፋኖ ወላጆችና የታጋይ
ቤተሰቦች!
*ለመላው የአማራ ትግል ደጋፊወችና ኢትዮጵያውያን በሙሉ!
እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ! አዲሱ አመት የአማራ ህዝብ ትግል በድል የሚጠናቀቅበት እንዲሆን እንመኛለን።
እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ ለአመታት በጦርነት ቀንበር ውስጥ ሆኖ ኑሮውን እየገፋ ይገኛል። ንሥር ብሮድካስት ኮርፖሬሽንም በአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን እና እየተፈፀ ያለውን ጥቃት አስመልክቶ አማራው እራሱን እንዲያነቃና እራሱን ከጥቃት መከላከል እንዲችል ከ2013 ዓ. ም ጀምሮ ላለፍት አመታት እለታዊ መረጃወችን በየቀኑ በማቅረብ አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቷል። ይህን አረመኔና አገር አጥፊ ስርዓት በማጋለጥና ወገናችን ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት ለማስቆም በሚደረገው እርብርብ ንሥር ብሮድካስት የራሱን ሚና ተጫውቷል። ሆኖም ከ2018 ጀምሮ የእለታዊ ዜና ስርጭት ፕሮግራማችን ስለማይኖር እሰከ አሁን ስትከተሉን የነበራችሁ ተከታዮቻችንና እንዲሁም መረጃ ስታደርሱን የነበራችሁ ምንጮቻችንን ከልብ እያመሰገን ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ሌሎች ተመሳሳይ የትግል ሚዲያወችን እንድትጠቀሙና እንድትከተሉ በአክብሮት እናሳስባለን። ለወደፊትም ከድል በሗላ በሌሎች የአማራ ትግል ታሪክ ዶክመንታሪወች እና ለነፃነት የተዋደቁ ወገኖቻችን በሚዘክሩ ፕሮግራሞች ተመልሰን እንደምንገናኝ ለማስታወስ እንወዳለን።
በመጨረሻም
የተጀመረው የህልውና ትግል ከግብ እንዲደርስ እና በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሁሉም አማራ እና የአማራ ትግል ደጋፊ በጋራ እንዲቆም፣ በአንድነትና በህብረት እንዲታገል እናሳስባለን።
ድል ለጀግናው የአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!
መልካም አዲስ ዓመት!
ንሥር ብሮድካስት ኮርፖሬሽን
ዕረቡ ዻጉሜ 5/2017 ዓ.ም

AM







