
የባንክ ሒሳብ ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር ለኔ ምን ጠቀሜታ አለው ብለው ያስባሉ?
• አስተማማኝ ደህንነት፦ ሂሳብዎ ከባዮሜትሪክ መረጃዎ ጋር ስለሚያያዝ ፤ በእርስዎ ስም ተመሳስሎ በሀሰተኛ ሰነድ የሚሞከርን ስርቆት ይቀንሳል።
• በባንክ እና በተበዳሪ መካከል መተማመን ፦ ባንኮች የእርስዎ ትክክለኛ መረጃ ስለሚኖራቸውና መተማመንን ስለሚያሰፍን የብድር አገልግሎትን ለማግኘት ቀላል ያደርገዋል።
• ሁሉንም ባንክ በአንድ ማንነት፦ በፋይዳ መታወቂያ የሁሉንም ባንኮች መረጃዎን የተናበበ እና ሂሳብዎን በተቀናጀ መንገድ ማስተዳደር ያስችላል።
• ባንክ መሄድ ሳያስፈልግዎ ፦ ባንክ መሄድ ሳያስፈልግዎ፣ በዲጂታል የማንነት ማረጋገጫ (eKYC) ብቻ የባንክ አገልግሎቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ማግኘት ይችላሉ።
የባንክ ሂሳብዎን ከፋይዳ ጋር ለማስተሳሰር፡ id.et/connect ላይ ይግቡ።

AM












