Mesay Mekonnen
1K posts

Mesay Mekonnen
@mamamesay
News anchor
Alexandria, VA Katılım Ağustos 2011
317 Takip Edilen248.4K Takipçiler

በጠዋት ስነሳ የዋትሳፕና የሜሴንጀር ሳጥኖቼ በመልዕክት ተጨናንቀው አገኘኋቸው። በሁለቱም ሳጥኖች የመጡት መልዕክቶች ስለአንድ ጉዳይ መሆኑ ትኩረቴን ሳበው። አነበብኩት። ሳቅና ንዴት ተፈራረቁብኝ። ሳቁ የማያባራው የብልጽግና ድራማ መሆኑ ነው። ንዴቱ ደግሞ አሁንም በዚህ ኋላቀር ፓርቲ ቀሽም ድራማ ላይ የምንመሰጥበት ነገር ነው። ብልጽግና ብዙ ድራማዎችን ተጫውቷል። አያሌ ቲያትሮችን ተውኗል። በየጊዜው አቅጣጫና ትኩረት ለማስቀየስ ይረዳሉ ያላቸውን አጀንዳዎችን ወደ መድረክ ወርውሯቸዋል። ተጠልፈው የተወሰዱ አልነበሩም ማለት አይቻልም። የማምሻ እድሜ ለሚለምነው ብልጽግና ማወናበድና ማደናገር የህልውናው የጀርባ አጥንት ነው። እውነት እዚያ መንደር ተቀብራለች። ውሸት ነግሳለች። 8 ዓመት ከበቂ ጊዜ በላይ ነው። ብልጽግና የሚሉትን ወለፈንዲ ፓርቲ ለመረዳት አሁንም ግራ የገባን ካለን ችግሩ ከራሳችን አቅመቢስነትና ደካማ የአእምሮ ውቅር ጋር የተያያዘ ስለሚሆን በጊዜ ወደ ሳይካትሪስት መሄድ ይኖርብናል።
የዛሬው የብልጽግና ማውናበጃ አጀንዳ ደግሞ የአዲስ አበባ ጉዳይ ሆኗል። አዲስ አጀንዳ አይደለም። ብልጽግና ብርድ ብርድ ሲለው የሚመዘው ነው። አዲስ አበባን በኦሮሚያ ስር የማድረግ ፕሮጀክት በሚል ርዕስ የተበተነው ወረቀት በእርግጥም አብይ አህመድ ጥልቅ በሆነ ፍርሃት ውስጥ እንደሚገኝ ጠቋሚ ነው። ወለጋ ድረስ ዘልቆ በአማራና በኦሮሞ መሃል ጥላቻን ጠምቆ መጣ። ከሚሴ ተጉዞም የሁለቱን ማህበረሰቦች የግጭት አጀንዳ ለኩሶ ተመለሰ። እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል - የሚል ምላሽ ቢሰጠውም ተስፋ የሚቆርጥ አልሆነም። ለጥላቻው ማርከሻ፥ ለግጭት አጀንዳው ማምከኛ የሚሆነው የአንድነት ድምጽ እየረበሸው ነው። ድም ድም እያለ ከቤተመንግስት ደጃፍ እየቀረበ የመጣው የለውጥ ድምጽ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ዘፍቆታል። አሁን ደግሞ የምር የሆነው ለውጥ እየመጣ ነው። በጦር መሳሪያ ብዛት፥ በሰራዊት ክምችት፥ በፕሮፕጋንዳ ጩኸት፥ በድራማና ቲያትር የማይቀለበስ የኢትዮጵያ ህዝብ የለውጥ ውሳኔ ገፍቶ ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
አዲስ አበባን ለኦሮሚያ ክልል የማድረግ ፕሮጀክት አስቂኝ የፈጠራ ድርሰት ነው። የኦሮሞና የአማራን ህዝብ አንድነት ያፈርሳል በሚል በአብይ አህመድ በኩል ተስፋ የተደረገበት አጀንዳ ነው። በልዩ ሁኔታ ተቀምሞ የተዘጋጀ ሰነድ ነው። ለፖለቲካው ባይተዋር የሆነን ሰው ጠልፎ ይወስዳል። የአብይ አህመድ ሸፍጥና ተንኮል ላልተገለጠለትም ትኩረት የሚስብ መሆኑ አይቀርም። ላለመንቃት ለጥ ብሎ መተኛትን ለመረጠም ሰነዱን የእውነት አድርጎ ሊቀበለው እንደሚችል አያጠራጥርም። በተረፈ የዛሬው የብልጽግና ሙከራ ከሁለት ቀናት ያልዘለለ እድሜ ሳይኖረው በኖ የሚጠፋ እንደሚሆን አምናለሁ። ከአዲስ አበባ አጀንዳ በላይ የሚያስቅጨንቅ የኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ከፊታችን ተደቅኗል። የማናልፈው፥ የማንሻገረው፥ ተጋፍጠን፥ መስዋዕትነትን ከፍለን የምናድነው ግዙፍ የህልውና አጀንዳ አለብን። ኢትዮጵያን በማዳን ውስጥ የአዲስ አበባ ጉዳይ መልስ ያገኛል። ህልውናችንን ከተጋረጠበት ጥልቅ አደጋ በመቀልበስ የሚረጋገጥ የኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅም ይኖራል። ይኸው ነው!!
AM

ም/ጠ ሚኒስትሩ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋናው መስሪያ ቤት በተዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ ተገኙ የሚል ዜና ስመለከት ነገሩ እንዴት ነው? የሚለው የኩኩ ሰብስቤ ሙዚቃ ትዝ አለኝ። ዘንድሮ ብልጽግና እንደፓርቲ ኢፍጣርን ልዩ የምርጫ መቀስቀሻ መድረክ አድርጎ እየሰራበት እንደሆነ ባለፉት ሶስት ሳምንታት የተደረጉትን ክስተቶች በማስታወስ መረዳት ይቻላል። የተለመደውን መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚለውን ክሊሼ እዚህ መሰንቀር አያስፈልግም። አብይ አህመድ የሚሉት ውል የሌለው፡ በጨበጣ ሀገር የሚመራ ሰው ስለሚያደርገውና ስለሚናገረው ነገር ከህግና ከስርዓት አንጻር መለካትና መመዘን ትርፉ ድካም ነው።
ሰውዬው በዋል ፈሰስ ነው። ለህግም ለሞራላዊ እሴትም፥ ለየትኛውም ዲሲፕሊን ተገዢ መሆን የማይፈልግ፥ ስሜት የሚነዳው፥ ጀብደኝነት መገለጫው የሆነ እጅግ ደካማና ጨካኝ ሰው ነው። ኢፍጣርን የፖለቲካው አጀንዳ ማጠንጠኛ ያደረገው ለተንኮልና ለግጭት እንጂ ለእምነቱ ተከታዮች ያለውን ክብር ለማሳየት እንዳልሆነ ልብና ኩላሊትን ሳንመረምር በቀላሉ የምንረዳው ነገር ነው። የአብይ እያንዳንዷ እርምጃ ስለምን ሰበብ ምክንያት እንደምትደረግ የተሰውረበት ያለ አይመስለኝም።
ለማንኛውም በደህነንት መስሪያ ቤቱ የኢፍጣር ስነስርዓት የሚደረግበት ምክንያት አልገባኝም። በየሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይም ሊደረግ እንደሚችል ጠቋሚ ነገር ነው። አብይም እንደህዳሴ ዋንጫ በየክልሉ እየዞረ ከብስክሌት መንዳት በተጨማሪ የሰሞኑ ዋና ተግባሩ የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ በመታደም የሚያሳየው ተራ የታይታ እንቅስቃሴ ነው። በዚህ ዓመት የሮመዳን ጾምና የአብይ ጾም ተከታትለው ሲጀምሩ የአብይ አህመድ የመልካም ምኞት መግለጫ የተሰማው ለአንደኛው የጾም ጅማሬ መሆኑን ለታዘበ፥ ሰውዬው በእያንዳንዱ ንግግሩና መግለጫው የሚጠምቀውን ጥላቻ በቀላሉ የሚረዳው ነው። በመሰረቱ አብይ አህመድ ሙስሊም አይደለም። የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ እንደሆነ ጸልየን ቤተመንግስት አስገባነው የሚሉ ፓስተሮችን ምስክርነት በማስረጃ ማቅረብ ይቻላል።
በእርግጥ አብይ አህመድ እንደመድረኩ ነው። ባለፈው ጀርመን ሳይጋበዝ በሄደበት ጉዞ በርሊን ላይ በተጠራ የፕሮቴስታንት ትልቅ መድረክ ላይ ''እኔን የሚጠሉኝ የኢየሱስን ጌታነት በተቀበልኩበት የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይነቴ ነው'' ያለበት ንግግሩ የሰውዬውን ማንነትና ምንነት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ኦርቶዶክሶች የሚቃወሙኝ ከሙስሊም የተገኘሁ የመጀመሪያው መሪ ስለሆንኩ ነው ያለበትን የቆየ ንግግሩን ማስታወስ ተገቢ ነው። ሁለቱ ሲኖዶሶች ተስማምተው ወደ አንድነቱ ሲመጡ ታሪክ ጠልፎ የሱ ሽምግልና ውጤት አድርጎ በተናገረበት መድረክ ላይ ''ኦርቶዶክስ ሀገር ናት።'' የሚል ስብከት ሲያሰማ ምን እንደፈለገ ግልጽ የሆነ ጉዳይ ነበር። እሱ የትኛውንም መሆን ይችላል። የትኛውንም መሆን ሲፈልግ ግን ለፖለቲካው ሸፍጥና ግጭት ለማዋለድ እንጂ ለመልካም ነገር እንዳልሆነ ለመረዳት የሚቸግር አይደለም።
አብይ አህመድ ፕሮአቴስታንትም አይደለም። ወደስልጣን እንደመጣ አፈራርሶ በራሱ አምሳያ የጠፈጠፈው የወንጌላውያን ህብረት ተቋም የመጀመሪያው ሰለባ ነው። እሱ ሙስሊምም አይደለም። በቴሌቪዥን በተላለፈ መድረክ መጅሊስ ጠልፎ የራሱን መጅሊስ ያቋቋመ ጀብደኛ ነው። እሱ ኦርቶዶክስም አይደለም። መፈንቅለ ሲኖዶስ አስደርጎ የራሱን ጳጳሳት ቤተክህነት በማስገባት ቤተክርስቲያኒቱን በእጁ ያስገባበት እርምጃው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። እሱ ሰባት ቀንድ ያለው፥ ሴጣን ላዩ ላይ የሰፈረበት አጋንንት ነው። ሰው ሲደሰት የሚከፋው፥ ሰው ሲከፋው የሚደሰት ክፉ መንፈስ ውስጡ የሞላው የእርግማን ውጤት ነው። በአንድ ሳምንት ውስጥ ኦርቶዶክሶች አርሲ ላይ ሲጨፈጨፉ፥ ሙስሊሞች አቤ ዶንጎሮ ላይ በጅምላ ሲገደሉ አንዲት ብጣሽ የሀዘን መግለጫ የማያወጣ፥ በየኢፍጣሩ እየዞረ ቲያትር የሚሰራ መሪ በእርግጥም የሴጣኖች አለቃ እንጂ ሌላ ምን ይባላል?
AM

በውስጥ መስመር የተላከልኝን እንደወረደ ላካፍላችሁ
በአዳማ/ናዝሬት በገንደሃራ ዛሬ በ25/06/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 በኋላ የፀጥታ አካላት የአማራን ቤት ለይተው ፍተሻ ሊያደርጉ ስለሆነ በአካባቢው ላይ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ። በቤቱ ወርቅም፣ብርም ያስቀመጠ ካለ እንዲያሸሽ ንገርልን የሚል መረጃ ደርሶኛል። ይህ ከመሆኑ በፊት ሰሞኑን ቤት ለቤት እየዞሩ ዲጅታል መታወቂያ ያለውና የሌለውን እየመዘገቡ እንደነበር ታውቋል። ቤት ለቤት ፍተሻው በሁሉም ቀበሌዎች የሚቀጥል መሆኑ ተረጋግጧል። ስለዚህ ጥንቃቄ ይደረግ።
AM

የመርካቶው ኪስ አውላቂ ሰውዬ የአብይ አህመድን የባህር በር አጀንዳ የማይደግፍ - ከፓርቲነት መሰረዝ እንዳለበት መናገሩን ሰማሁ። በስሙ ነው የጠራሁት። ባህሪውን የሚገልጽ ስም ነው። ምናልባት የመርካቶ ኪስ አውላቂ ምን ይመስላል የሚለውን ለማታውቁ ይህ ግለሰብ የሚያደርገውንና የሚናገረውን ይመስላል ነው በአጭሩ ሲመለስ። ሰውዬው በኮፍያ ስር ተደብቆ እንደሚመነትፍ የናዝሬት ሌባ ዓይነትም ባህሪ አለበት። ሙልጭ ያለ ወመኔ ነው። ሲናገር ስነስርዓት የለውም። አፉም ባለጌ ነው። ሰፈር ውስጥ እናቶች 'መደዴ' እያሉ የሚሰድቡት ዓይነት። የምርጫ ክርክር በተባለው የቅርብ ጊዜው አስቂኝ መድረክ ላይ አይዶሎጂ የለንም እያለ - ዓይኑን እያጉረጠረጠ ሲናገር ካየሁት በኋላ አሁንስ ለይቶለታል- እጁን ይዞ አማኑዔል የሚወስደው የቅርብ ሰው የለውም ወይ የሚል ጥያቄ ነበር ያነሳሁት። የኢዜማን ማለያ አጥልቆ ለብልጽግና ደምስሩ እስኪገተር ጥብቅና የሚቆመው ነገር እጅግ አስደማሚ ነው። ስራ ቀይሮ ሽንት ቤት ማስመጠጥና የጓሮ አትክልት ውሃ ማጠጣት ሃላፊ የሚል መደብ ላይ ከወጣ ወዲህ ደግሞ ብሶበታል። ሲበዛ ክብረ ቢስ ነው። ለልጆቹ አዘንኩኝ። ብልጽግናን ስንገላገል ገጻቸው ከዓይናችን ስር ከሚጠፉና ድምጻቸው ከጆሮአችን ከሚርቁ ድኩማን አንዱ ይህ ሰው እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።
AM


አብይ አህመድ መሳሪያ ፍለጋ አዘርባጃን መሄዱ ተሰምቷል። መቼም አዘርባጃን ከመሳሪያ ሌላ ምንም ጉዳይ ኖሮ የሚኬድባት ሀገር አይደለችም። ተመስገን ጥሩነህ የውሃ መንገድ አድርጎ ተመላልሶባታል። የምስራቅ ጎጃምን ችግር መፍታት ያልቻለው ተመስገን አዘርባጃን መሳሪያ እንድትሰጥ ለማግባባት በአብይ ተልዕኮ ተሰጥቶት ደጅ ሲጠና እንደነበረ በቅርበት የሚታወቅ ነው። አብይ አህመድ ከዚህች ሀገር በተደጋጋሚ መሳሪያ ሲሸምት እንደነበረ ከዚህ በፊት በርካታ ሪፖርቶች ወጥተዋል። ከአንድ ዓመት በፊት ከፍተኛ ከባድ መሳሪያዎች በሶስት መርከቦች ተጭነው በሜዲትራኒያን ባህር በኩል ሲያመሩ በኤርትራ መንግስት ተይዘው መሳሪዎቹ ሲወረሱ መርከበኞቹ በድርድር መፈታታቸው ይታወሳል። በዚህ የተበሳጨው አብይ አህመድ በአፍሪካን ህብረት ጭምር 'መሳሪያዬን መልሱልኝ' የሚል ተማጽዕኖ ለኤርትራ ባለስልጣንት ቢልክም 'እንትንህን ላስ' የሚል ምላሽ ተሰጥቶት እንደነበረ አስታውሳለሁ።
የአብይ የአዘርባጃን ጉዞ አሁንም መሳሪያ ለማግኘት ነው። በግዢ ይሁን በልመና የሚታወቅ ነገር የለም። ከፍተኛ የጦር መሳሪያ እጥረት ገጥሞታል። አብይ አህመድ ሶስት ሃይሎችን ያስታጥቃል። የራሱን ሰራዊት፥ ፋኖንና ኦላን የሚያስታጥቅ በመሆኑ አሁን ከፍተኛ ክፍተት ተፈጥሮበታል። ጠዋት ተመርቶ ከሰዓት መርካቶ እንደሚባለው፥ ምንም እጅ ያልነካቸው የተወለወሉ መሳሪያዎችን ጠዋት የአብይ ሰራዊት ይይዛቸዋል፥ ከሰዓት ፋኖ ተረክቦ ይታጠቃቸዋል። ለማንኛውም የአብይ የአዘርባጃን ጉዞ መሳሪያውን መግዛት ብቻ ሳይሆን እንዴት ወደ ኢትዮጵያ ይድረሳል የሚለውንም ለመነጋገር ጭምር ነው። የኢትዮጵያውንን ጉሮሮ እያደረቀ፥ ከቀለባቸው ላይ እየነጠቀ በውጭ ምንዛሪ መሳሪያ ይሸምታል፥ መዳረሻው ግን ከኤርትራ ምድር እየሆነበት ተቸግሯል። ለሁለተኛ ጊዜ ስህተት መስራት አልፈለገም። ይህንንም መፍትሄ ለማፈላልግ የታለመ ጉዞ ይሆናል የሚል ግምት መውሰዱ ስህተት ላይ አይጥልም።
ሰውዬው ግን እንዴት ባለ የጦርነት ልክፍት ተይዟል? አንድም ቀን ያለጦርነት ሀገር መምራት ሳይችል ስምንት ዓመቱን ደፈነ። የፖለቲካ መፍትሄ እሱ ዘንድ ሀጢያት ነው። ያስቀስፋል። በጡንቻ ፍለጠው ቁረጠው፥ በለውና አሳደው ናቸው በዲክሽነሪው ውስጥ የሚገኙ ቃላት። ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ቀምተህ መሳሪያ ገዝተህ መልሰህ ይህን ህዝብ የምትፈጅበት አእምሮ ካለ ያም የአብይ አህመድ ብቻ ነው። ከዚህ ህዝብ ላይ የምትወስደው ገንዘብ ከአስክሬን ላይ ከፈኑን የመግፈፍ ያህል የሚዘገንን ነገር ግን ለአብይ አህመድ እጅግ ቀላል የሆነ እርምጃ ነው።
AM

የአብይ አህመድ ተውኔት ልክ እንደህንድ ፊልም ነው። ቀጥሎ የሚታየውን አክሽን በቀላሉ እንደምትገምቱት የህንድ ፊልም የአብይ አህመድ ድራማም የሚቀጥለውን ድርጊት አስቀድሞ ለማወቅ የሚቸግር አይደለም። ለአገኘሁ ተሻገር በአንድ ስልክ የወልቃይትን የምርጫ ጉዳይ የተመለከተ እንዲህ አድርግ ይለዋል። ለምርጫ ቦርዷ ሴትዮ ወዲያውኑ የምታወጣውን ውሳኔ ይነግራታል። ከዚያም እነበለጠ ሞላ የደስታ መግለጫ እንዲያወጡ ያዛቸዋል። ለጌታቸው ረዳ ደግሞ አንድ ቀን ቆይተህ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርብ የሚል መመሪያ ይሰጠዋል። ለብልጽግና ዳኞች ሚናቸውን እንዳይረሱና የተሰጣቸውን ገጸባህሪያ እንዳያዛንፉ ያሳስባቸዋል። እንደታዘዙት የእግድ ውሳኔ ያስተላልፋሉ። ይሄው ነው። ሁሉም ቦታ አብይ አህመድ ነው የሚወስነው። የተፈለገው ምርጫውን ማዳመቅ ነው። ህዝብ ትኩረት የነፈገውን የጨረባ ምርጫ በዚህ መልኩ አጀንዳ ለማድረግ የተቀመረ የበሻሻ ሰፈር ተውኔት ነው። ፊልሙ የተቃጠለ ተውኔት።
AM

ጋሻው መርሻ የሚሉት ሰው ለቢቢሲ የሰጠውን ቃለመጠይቅ አነበብኩት። ይሄን ሰሞን ተንቀዥቅዧል። ለጤና ያድርግለት። ለአቅመ ፖለቲካ አለመድረሱ የተጋለጠበትን ቃለመጠይቅ አንብቡት ብሎ መጋበዙ ደግሞ በነውር ማጌጥን የሚኮራበት እንደሆነ ማሳያ ነው። እነክርስቲያን ታደለና ዶ/ር ደሳለኝ ላይ የወረወረው ክስ ምን ያህል ደሙ ውስጥ ክፋትና ተንኮል እንደሚዘዋወሩ ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው። እጅግ ሲበዛ መጥፎ ሰው ነው። ይህቺ ቀደም ቀደም ደብቁኝን ማምጣቷ አይቀርም። የብልጽግናን የሀሰት ክስ ዶሴ አንጠልጥሎ ይዞራል። በቢቢሲው ቃለመጠይቅ የተረዳሁት ነገር ቢኖር 'ፖለቲካ በደረሰበት እንዳይደርስ' መደረግ ያለበት ሰው መሆኑን ነው። ጉርምስናውን አልጨረሰም። ቦዘኔነት ይንጸባረቅበታል። ብስለት የጎደለው፥ ማስተዋል የራቀው፥ መደንፋትን እንደትልቅ ብቃት የሚቆጥር ደካማ ፍጡር ነው።
የቢቢሲዋ ጋዜጠኛ ላብ በላብ ስታደርገው ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘግቶ ቃለመጠይቁን አቋርጧል። ለብልጽግና ያለውን ታማኝነት ለማሳየት የሄደበት ርቀት አጃኢብ የሚያሰኝ ነው። እሱንና ጓደኞቹን አብይ አህመድ ምን ዓይነት መርፌ እንደወጋቸው አናውቅም። ስሙን መነቀስ ነው የቀራቸው። በስሙ መማል መጀመራቸውን ሰምቼአለሁ። በቅርቡ ፎቶግራፉን እንደክታብ አንገታቸው ላይ ማንጠልጠላቸው አይቀርም። እንደግብጾቹ ንጉሳውያን አሽከሮች፥ ጌቶቻቸው ሲሞቱ ከነህይወታቸው አብረው እንደሚቀበሩት ዓይነት ፍጹም ታማኝ ገረድ መሆናቸውን ይበልጥ እየተረዳን መጥተናል። ጋሻውና ጓደኞቹ እንዲህ ያንቀዠቀዣቸው ያለምክንያት አይደለም። ከብልጽግና በላይ ለብልጽግና የጉሮሮአቸው ግድግዳ እስኪሰነጠቅ የሚጮሁት ወደው አይደለም። ብልጽግና ከተወገደ ወላጅ አልባ ሆነው መቅረታቸው ከወዲሁ አስጨንቋቸው መሆኑን በሚገባ አውቀናል።
ይልቅስ በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ያጋጫችሁት የውስኪ መለኪያ ድምጹ ከጆሮአችን ሳይጠፋ ውሳኔው በፍርድ ቤት ታግዷል። የአብይ አህመድ ቲያትር ማድመቂያ መሆናችሁን ህዝብ እየታዘባችሁ ነው።
AM

የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳኑ አማጺ ቡድን አራት መሪዎች ላይ ማዕቀብ መጣሉን አስታውቋል። መሀመድ ደጋሎን ጨምሮ ማዕቀብ የተጣለባቸው አራቱ የፈጥኖ ደራሽ ሰራዊት አመራሮች በጅምላ ግድያና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች የሚጠየቁ በመሆናቸው ነው። ይህ የመንግስታቱ ድርጅት ውሳኔ ለአብይ አህመድ አገዛዝ ድንጋጤን የሚፈጥር ይሆናል። በሱዳን ጉዳይ ጣልቃ ገብቶና የጦር ሰፈር ለዚሁ አማጺ ቡድን የሰጠው አብይ አህመድ ከመንግስታቱ ድርጅት ቁንጥጫ ይጠብቀዋል። አሜሪካንም በሱዳኑ ግጭት እጃቸውን ባስገቡ አካላት ላይ ማዕቀብ ልትጥል እየመከረች መሆኗ ተሰምቷል። አብይ በአሜሪካን የማዕቀብ አርጩሜ መገረፉ የማይቀር ነው። በቅጥረኝነት ለሚያገለግላት ሚጢጢዬ ሀገር ኤሜሬትስ ብሎ ታላቋን ኢትዮጵያ ያዋረደና ያስጠቃ የዘመናችን ክፉ ዲያቢሎስ ነው - አብይ አህመድ።
AM

ይህ ከታች የምታዳምጡት ብርሃኑ ነጋ በአሁኑ ብርሃኑ ነጋ ተቀርጥፎ ተበልቷል። ሰው ራሱን በራሱ ሲያጠፋ እንዲህ ነው። እነዚያ የዲሲ መድረኮች ላይ፥ በቨርጂኒያ አዳራሾች ውስጥ፥ በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች ሲስተጋቡ የነበሩ የብርሃኑ የፍትህና የነጻነት ድምጾች አየር ላይ ተነዋል። ይህን የመሰለ ስሜት ገዢና ሰው ሰው የሚሸት መልዕክት ያሰማን አንደበት፡ የአብይ አህመድን አረመኔያዊ አገዛዝ ሲያገለግልና ጥብቅና ሲቆም መስማት ያስደነግጣል። ለአሁኑ ብርሃኑ ነጋ የምናቀርብለት አንድ ጥያቄ የትላንቱን ብርሃኑ ነጋ የት አደረከው? ውጠኸውም ከሆነ ትፋውና ለኢትዮጵያ ይድረስላት የሚል ነው።
AM

የኦብን(አብን) ልጆች በምርጫ ቦርድ ውሳኔ መለኪያቸውን እያጋጩ ደስታቸውን እየገለጹ ነው። በዚህ ደረጃ ለፖለቲካ ባይተዋር ይሆናሉ ብዬ አልገመትኩም። ምንጣፍ ጎታችነት እንደዚህ አቅል በሚያስትና በሚያዝረከርክ ስብዕና በአደባባይ እዩኝ - ስሙኝ ያሰኛቸዋል የሚል ጥርጣሬ እንኳን አልነበረኝም። ለካንስ መገረድን እስከቀራኒዮ ቃል የገቡለት ውሳኔያቸው ነው? ያሳዝናል። አብኖች የት ሊወዳደሩ ነው ምርጫ ውስጥ የሚገቡት የሚል ጥያቄ ጭሮብኝ ነበር። አሁን ተመለሰልኝ። በራያና ወልቃይት ምርጫ ጣቢያዎች ተወዳድረው ምክር ቤት በመግባት ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በፓርላማ የአብይ አህመድን ስልጣን ሊያዳምቁ መሆኑ የተገለጠልኝ አሁን ነው። የእነጣሂርና ጋሻው መርሻ ሩጫ ይህቺው ናት። በአብይ አህመድ ሰፌድ ላይ መንከባለል። ደግሞ አብይ አህመድን ተደግፈው፥ የኦህዴድ ብልጽግናን ቀለብ እየጎረሱ ሌላውን ለመፈረጅና ለመወንጀል መዳፈራቸው አስደማሚ ነው። የሞራልንና የህሊናን ጉዳይ አፈር ድሜ ካበሉት አምስት ክረምቶች አልፈዋል ለካ?!
AM

ኢትዮጵያ ውስጥ የህግ የበላይነት የለም። የህግ መወሰኛ፥ የህግ ተርጓሚ፥ የህግ አስፈጻሚ የሚባሉ ተቋማት ለይስሙላ እንጂ በተግባር የሉም። ኢትዮጵያ ውስጥ አብይ አህመድ የሚባል ሰው ነው ፈላጭ ቆራጭ። የዛሬው የምርጫ ቦርድ መግለጫ ላይ የፌደሬሽን ም/ቤት ስም ተጠቅሶ የወልቃይትና ራያ የምርጫ ሁኔታ ውሳኔ ማግኘቱን ስመለከት አብይ አህመድ የሚጫወተው ቁማር ነው የተገለጠልኝ። ሁለቱ ማህበረሰቦች የህልውና ጥያቄ እንዳላቸው በሚገልጹበት በዚህን ወቅት፥ የእርስ በእርስ ፍጥጫ ውስጥ እንዲገቡና የአብይ አህመድን የስልጣን ዘመን በሚያራዝም ግጭት ላይ እንዲጠመዱ የሚያደርግ አደገኛ ውሳኔ ነው። በአንደኛው ወገን የሚያስጨፍር፥ በሌላኛው ደግሞ ጸጉር የሚያስነጭ ሊሆን አይገባውም። ይህ የአብይ አህመድ መርዛማ ውሳኔ ነው። ተጣድፎ መቦረቅም፥ ተቻኩሎ መበሳጨትም የሚያስፈልግ አይደለም። ሁለቱም ወገኖች ከዚህ የአብይ አህመድ ወጥመድ ውስጥ ባለመግባትና የሁለቱም የህልውና አደጋ የሆነውን የብልጽግናውን ስርዓት በማስወገዱ ትግል ላይ ማተኮር ይገባቸዋል።
AM

አብይ አህመድ በሀዋሳ ሲሸልልና ሲፎክር ነበር። ከሶማሊያ እስከምጽዋ ሽብርተኝነትን የሚዋጋ ኢሊት ፎርስ ገንብተናል ይላል። ለአፍ መቼም ዳገት የለውም። የሚሉሽን ባልሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ - የገዛ ግዛቱ በሆነው ትግራይ ክልል ሰራዊቱ መግባት የማይችለው አብይ አህመድ ሶማሊያና ምጽዋ እንደርሳለን ሲል መቼም ክርስቲያኑ 'በስመአብ በወልድ' ብሎ ድንጋጤውን መግለጹ፥ ሙስሊሙም 'እስታፉሩላ' እያለ አምላኩን ምህረት መጠየቁ አይቀርም። ሰውዬው አቅመቢስነቱ ላይ እብደት ተጨምሮበት ነገር ዓለሙን ግልብጥብጥ አድርጎታል። ኢሊት ብሎ አሰልጥኖ ያሰማራው ሰራዊቱ ሸዋ ላይ በፋኖ እንደክምር እህል ሲወቃ የነበረው እኮ ባለፈው ሳምንት ነው። ትግራይ ክልልን ተሻግሮ ለመዋጋት ፍቃድ የሚጠይቅ አገዛዝ ከሶማሊያ እስከምጽዋ ሽብርተኝነትን እዋጋለሁ የሚል ተረት ተረት ሲያወራ መስማት የጆሮን ኮፈን የሚያሳምም ነው። ፌንጣ ብትቆጣ ክንፏን ታጣ ነው ነገሩ። የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች መሆኑ አይቀርም። ምጽዋና አሰብን ከሩቅ ሲመኝ አዲስ አበባን ሊነጥቅ እንደሚችል የተረዳው አይመስልም። እብሪት፥ ትዕቢት፥ ድንቁርና፥ ጀብደኝነት ልቡን ደፍኖታል።
AM

ብርሃኑ ነጋ ፍሬን በጥሷል። በእርግጥ የምሁርነት ካባውን አውልቆ ሙልጭ ያለ የብልጽግና ካድሬ ከሆነ ሰንብቷል። አሁን ግን ለየለት። እንጥፍጣፊ እንኳን አላስቀረም። ነገ ሁኔታዎች ስለሚቀየሩ ለመመለሺያው የሚሆኑ የተወሰኑ ነገሮችን በሆዱ ማቆየት አልፈለገም። ሁለመናውን ለብልጽግና አሳልፎ ሰጥቷል። ብርሃኑን በዚህ ደረጃ መግለጽ ከባድ ነው። ህሊና ካዳለጠ ለካንስ መመለሺያም የለውም?! በእርግጥም ብርሃኑ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ሆኗል። ብልጽግናዎች በሱ ልክ ለፓርቲያቸው እየሰሩ አይመስለኝም። ለምን ኢዜማ የሚባል ፓርቲ በህይወት እንዲቆይ እንደፈለገ አይገባኝም። ሰሞኑን የተለቀቀውን የዙም ውይይት በቁራጩ ለተለመለከተ ሰው ኢዜማ የሚባል ፓርቲ የመኖሩ ትርጉም አይገባውም። መሪው ስለብልጽግና አውርቶ አይጠግብም። ብርሃኑ የብልጽግና አጥር ሆኖ ብቅ ብሏል። ያውም የብረት አጥር። እንደሰማሁት ከሆነ ኢዜማን ሊሰናበት ነው። ምናልባት በመጪው ምርጫ ብልጽግናን ወክሎ ሊወዳደር ይሆን?
AM

የቱርኩ ፕሬዝዳንት በብልጽግናው መንደር ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ቸልሰዋል። ኤርዶጋን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በተለየ ተልዕኮ ነው። አቡዳቢና አዲስ አበባ ለመሄድ ነበር እቅዳቸው። የኤሜሬትሱ መሪ በጤንነት ችግር ምክንያት ኤርዶጋንን ማስተናገድ እንደማይችሉ በመገለጹ ጉዞው ተሰርዞ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ነው የመጡት። ሁለቱ ሀገራት ላይ ያተኮሩበት ምክንያት ከሱዳኑ ጦርነት ጋር የተያያዘ እንደሚሆን ለመደምደም የፖለቲካ ጠበብት መሆንን አይጠይቅም። ግልጽ የሆነ ጉዳይ ነው።
ኤሜሬትስ ሀገር እያፈረሰች መሆኗ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ አሳስቧል። ሊቢያ ስትፈርስ መዶሻ ስታቀብል የነበረችው ኤሜራትስ ናት። የመን ብትንትኗ ሲወጣ ቤኒዝን ስታርከፈክፍ ነበር። ሱዳንን ጀምራታለች። ልትጨርሳት ከጫፍ ደርሳለች። ሱዳንን ማፍረሺያ ፕሮጀክቷ ውስጥ ደግሞ አብይ አህመድ አለ። እንደፈለገች የምታዘው፥ ስትጠራው አቤት፥ ስትልከው ወዴት የሚልላት ታማኝ አሽከሯ አብይ አህመድ ነው። ይህ የሱዳን ጉዳይ እነቱርክንና ሳዑዲ አረቢያን ከተኙበት እንዲነቁ አድርጓቸዋል።
ባለፈው ሳምንት የሳዑዲ አረቢያው ከፍተኛ ባለስልጣን የመጡትም አብይ አህመድ ከኤሜራትስ ጎን ተሰልፎ ሱዳን ላይ ያነሳውን ሰይፍ ወደ አፎቱ እንዲያስገባ ለመምከርና ለማስጠንቀቅ ነው። የኤርዶጋንም አመጣጥ ለዚሁ ነው። ሌላ ነገር የለም። በአብይ አህመድ ናፍቆት እህል አልበላ ብሏቸው ስለተቸገሩ የመጡ አስመስለው ሊነግሩን የሚቃጣቸው የብልጽግና ዲጂታል ሰራዊት አባላት እንዳሉ እየታዘብኩ ነው። ከሁሉም የአብኑ ጣሂር መሀመድ ''የኢትዮጵያ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የተመሰከረበት ጉብኝት'' የሚል ልጥፍ ይዞ ሲመጣ ገርሞኝ የትላንቱን ጣሂር ማሰብ ጀመርኩ። ሰው በዚህ ደረጃ ቂልና ጅል ሲሆን ያስደምማል።
ለማንኛውም ኤርዶጋን በዲፕሎማሲያዊ አነጋገር አብይ አህመድን ''አርፈህ ተቀመጥ'' ብለውታል። አፍሪካ ቀንድ ላይ ችግር ማየት አንፈልግም ሲሉ ቆፍጠን ብለው ነግረውታል- ለቀጣናው ረባሽና በጥባጭ አብይ አህመድ። እንዲህ ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ጥፊ አይጣል ነው።
AM


