

Sputnik Ethiopia
9.8K posts

@sputnik_ethio
🇪🇹 ትኩስ እና ልዩ የአፍሪካ መረጃዎች፣ ትንታኔዎች እና አስተያየቶች ስለ አፍሪካ በእንግሊዘኛ ቋንቋ፤ @sputnik_africa



ኢትዮጵያ በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ከ10 ዓመት በኋላ የዓለም ገበያ ዋነኛ አቅራቢ ትሆናለች - ግብርና ሚኒስቴር 👉 አስረኛው ዓለም አቀፍ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ተከፍቷል፡፡ 🗣 ዘርፉ 200,000 ለሚጠጉ ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል እንደፈጠረ በመድረኩ ተገልጿል። 🗓 ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆየው ዐውደ ርዕይ ዓለም አቀፍ አቅራቢዎች ከኢትዮጵያ የዘርፉ ተዋናዮች ጋር የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት ነው ተብሏል።





ፖላንድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጽጌ ዱጉማንና ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ቪዛ ከለከለች 🥈 በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ በሴቶች 800 ሜትር የብር ሜዳሊያ በማሸነፍ በታሪክ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት እና ሌሎች የመካከለኛ ርቀት ሯጮች ሳሮን በርሄ፣ ሀረገወይን ካላዩ እና ሞሲሳ ስዩም በፖላንድ ቶሩን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንዳይሳተፉ ታግደዋል። 🇵🇱🇺🇸 የፖላንድ የቪዛ እገዳ ባሳለፍነው ጥር ወር በፍሎሪዳ ታላሃሲ ተዘጋጅቶ በነበረው የዓለም አትሌቲክስ የታዳጊዎች ሻምፒዮና ውድድር 14 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ከተከለከሉ በኋላ የመጣ ነው፡፡ 🇪🇹 እነዚህ ክልከላዎች ኢትዮጵያ ሜዳሊያ የምታገኝባቸው ውድድሮች እንዲቀንሱ የሚያደርጉ እና "ስፖርታዊ አፓርታይድ" እንደሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡









