GIRMA KASSA

24 posts

GIRMA KASSA

GIRMA KASSA

@wameraGK

Katılım Nisan 2024
19 Takip Edilen146 Takipçiler
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
አፋህዴዎች ፋኖዎችን ይቅርታ ቢጠይቁ ሊረዳቸው ይችላል #ግርማካሳ እስክንድር ነጋ ዙሪያው ያደረገው ፣ የሚሰማቸው አማካሪዎች እንጦሮሮስ ውስጥ እየከተቱት ያለ ይመስለኛል፡፡ ወይም ምክር የተለየ ሐሳብ የማይሰማ ግትርና stubborn ነው፡፡ እስቲ አስቡት እስክንድር ከአንድ አመት ተኩል በፊት የነበረውን የፖለቲካ ቁመናና አሁን ያለውን የፖለቲካ ቁመና !!! የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት መሪዎች ውይይት የሚባለውንና ትልቅ ተቃውሞና ውዝግብ ያስነሳዉን ከማድረጋቸው፣ በፊት እርስ በርስ ተነጋግረው እንደነበረ፣ ከነርሱ መካከልም፣ "ይቅርብን፣ ከሕዝብ ጋር ያጣላናል፣ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል" ብለው ተቃውሞ ያሰሙና ያልፈለጉ ፣ ምቾት ያልሰጣቸው እንደበሩ፣ እስክንድር ነጋ እራሱ ለኢትዮ360 በሰጠው አስተያየት አሳውቋል፡፡ "ግድ የለም፣ በኔ ይሁንባችሁ፣ ለሚሆነው ነገር እኔ ሃላፊነት እወስዳለሁ" ብሎ ነው፣ ሌሎች ባይስማሙም፣ ሌሎች ላይ ጫና ፈጥሮ ወደዚህ ሂደት የተገባው፡፡ እስክንድር በድርጅቱ ውስጥ አምባገነን መሆኑን ከዚህ መረዳት ይችላል፡፡ ማይክሮ ማኔጅ የሚያደረግ ሰው ነው፡፡ የዳዎንቱ ስብሰባ፣ በሚስጥር ተደብቆ የተያዘ ስብሰባ ነበር፡፡ ሆኖም መረጃው አፈትልኮ መውጣቱን ተከትሎ፣ አፋህድ ከአገዛዙ ጋር ድርድር ጀመረ የሚለው ወሬ መናፈስ ጀመረ፡፡ ውስጥ ውስጡን በነ እስክንድር ላይ እሳት ተቀጣጠለ፡፡ በዚህ ጊዜ የአፋህዴ መሪዎች ወደ ሜዲያው ወጥተው ነገሩን ማርገብ፣ ማስተባበያ መስጠት ነበረባቸው፡፡ እስክንድር ነጋ በኢትዮ360 ቀረበ፡፡ "አዎን ከአራት አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ተገናኘትን ተወያይተናል" ሲል፣ በሚስጥር ያደረጉትን ንግግሩ መደረጉን አመነ፡፡ በፊት ውስጥ ውስጡን ነበር ወሬው ይወራ የነበረው፡፡ እስክንድር ነጋ በውስጥ ይወራ የነበረውን በይፋ እውነት እንደሆነ አረጋገጠ፡፡ "አዎን ውይይት አድርገናል፡፡ ሆኖም ውይይት እንጂ ድርድር አላደረግንም፣ ከብልጽግና ጋር አልተገናኘንም፡፡ ድርድር አደረጉ የሚባለው ውሸት" ነው አለ፡፡ በአንጻሩ የአገዛዙ ሜዲያዎች እየተቀባበሉ፣ ከፋኖ ጋር ድርድር እንደተጀመረ መናገር ጀመሩ፡፡ ገለልተኛ ሜዲያዎች ሳይቀሩ፣ እነ መሰረት ሜዲያ፣ ዋዜማ ድርድር በአለም አቀፍ ድርጅቶ በኩል እንደተደረገ በመግለጽ ዘገባዎችን ሰሩ፡፡ ሜዲያዎቹ፣ ገለልተኛ ሜዲያዎች ሳይቀሩ ዋሽተዋል በሚል የአፋህዴ መሪዎች በየሜዲያው እየቀረቡ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት ቀጠሉ፡፡ እስክንድር ነጋ በኢትዮ360 ሶስት ጊዜ፣ ከደረጄ ሃብተወልድ ጋር፣ እንዲሁም ከኢኤምኤስ ጋር ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ ፣ ሲደመር አምስት ቃለ መጠይቆችን አድርጓል፡፡ የአፋህዴ የፖለቲካ ዘር ሃላፊ ነኝ የሚለው ረ/ፕ ጌታ አስራደ ከአንከር ሜዲያና ከኢትዮፎከስ (በለጠ ካሳ) ጋር ቀርቦ ገለጻ ሰጥቷል፡፡ ማስረሻ ሰጤ በአዲስ ሜዲያ ላይ ቀርቧል፡፡ ሁሉም ሲደመሩ የአፋህዴ መሪዎች ስምንት ቃለ ምልልሶችን አድርገዋል፡፡ ያ ብቻ አይደለም፣ እስክንድር ነጋ ረጅም ሰዓት በቲክቶኮ ገለጻ ሲሰጥ ነበር፡፡ በትዊተርም እንደዚሁ ተመሳሳይ ገለጻዎች ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል፡፡ ይሁ ሁሉ የሜድያ ጋጋታ ለምን ? የሰሩት ስራ እጅግ በጣም ትልቅ ጉዳት እንዳመጣ ስለተረዱ ነው፡፡ ሆኖም ተመሳሳይ ነገር እየደጋገሙ ለስምንት ጊዜ ከመናገር፣ ህዝብን የሚያሳምን ትክክለኛ ነገር ያዘለ አንዲት ቃለ መጠይቅ ማድረጉ ይበቃ ነበር፡፡ የቃለ መጠይቆች ጋጋታ ያረገበው ምንም ነገር የለም፡፡ በኔ እምነት፣ መሳሳታቸውን፣ ችግር መፈጠሩን አምነው፣ "ምንም እንኳን አማራው ያለበትን ችግር ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማሳወቁ ጠቃሚ ቢሆንም፣ የፋኖን አንድነት እንዲወሳሰብ ባደረገና ከህዝብ በተደበቀ፣ የስብሰባው አጀንዳ ምን እንደሆነ ህዝብ ባልታወቀበት መልኩ የተደረገ ስብሰብ በመሆኑ ችግር መፈጠሩን ተገንዝበናል፡፡ በዳዎንቱ ስብሰባ ለተፈጠረው ውዝግብ፣ ግራ መጋባት፣ መከፋፈል፣ ለአገዛዙን ትልቅ የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ጥቅም እንዲያገኝ መደረጉና ይሄን ዘረኛ አገዛዝ ለማስወገድ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ፋኖዎችን ስሜት በጣም የጎዳ በመሆኑ፣ ትልቅ ስህተት መስራታችንን ተገንዝበናል፡፡ ብዙዎች በተለይም ፋኖዎች ተካድን ብለው ማዘናቸው ፣ መቆጣታቸውን ይገባናል፡፡ ለዚህም ይቅርታ እንጠይቃለን " ቢሉ፣ ከዚህ በኋላም ቅድሚያና ብቸኛ ስራቸው፣ ከሌሎች ፋኖዎች ጋር ተነጋገረው፣ ፋኖዎችን አንድ ማድረግ ላይ እንደሆነ፣ በግለሰብ ደረጃ መብታቸው ቢሆንም፣ ፋኖን ወከልን በሚል ምንም አይነት እንቅስቃሴና ንግግር ከማንም ጋር እንደማያደረጉ ቢያሳወቁ የተፈጠረውን ትልቅ ጉዳት ይቀንሱ ነበር፡፡ የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፣ የአማራ ፋኖ በወሎ ቤተ አማራ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ፣ የአማራ ፋኖ ወለጋ /ቢዛሞ እዝ በጋራ ባወጡት መግለጫ የዳዎንቱን ስብሰባ መቃወም አይደለም፣ ክህደት ሲሉ አውግዘውታል፡፡ እነዚህ አደረጃጀቶች ከ80% በላይ ፋኖዎችን ያቀፉ አደረጃጀቶች ናቸው፡፡ እውቁና ታላቁ የጦር መሪ ጀነራል ተፈራ ማሞ ድርጊትን ስህተት እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡ የተለያዩ እውቅ ፖለቲከኞች እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉ፣ በተለይም ለእስክንድር ነጋ እጅግ በጣም ቅርበት የነበራቸው እንደ ቀለብ ስዩም ያሉ፣ የሆነው ነገር ትልቅ ስህተት እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡ በሁሉም ጠቅላይ ግዛት ያሉ ፋኖዎች በአፋህዴ ውስጥ ያሉትን፣ የብልጽግና ሚሊሺያዎች ማለት ጀምረዋል፡፡ ህዝብ በጣም በጣም አዋረዱን እያለ ነው፡፡ ፋኖዎች እጅግ በጣም ተቆጥተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ እነ እስክንድር ትሁት ሆነው፣ ስህተታቸውን አምነው፣ ከግትርነትና እልህ ወጥተው፣ በጨዋነት ነገሩን ካላረገቡት፣ አካሄዳቸው ሜዳ ላይ ካሉት ፋኖዎች ጋር ካላደረጉ፣ በአማራ ክልል እንዴት ሊቀጥሉ እንደሚችሉ አላውቅም፡፡ ምን አልባት እጆቻቸውን ለብልጽግና ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
AM
4
0
2
311
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
አሁን እየተጠበቀ ያለው ሸዋ ነው #ግርማካሳ ከአንድ አመት ተኩል በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ አደረጃጀቶች ነበሩ፡፡ አሁንም በጠቅላይ ግዛት ደረጃ እየተሰባሰቡ ነው፡፡ የጎጃም፣ ወሎና ጎንደር ፋኖዎች በጠቅላይ ግዛት ደረጃ አንድ ሆነዋል፡፡ # በጠቅላይ ግዛት ደረጃ የተለያዩ የጎጃም አደረጃጀቶች በአንድ ላይ መጥተው፣ የአማራ ፋኖ ጎጃም እዝ፣ በኋላ ስሙ የአማራ ፋኖ በጎጃም የሆነውን መሰረቱ፡፡ ጎጃምን አንድ አደረጃጀት የተመሰረተው የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ/ም ነበር፡፡ በጎጃም እምብርት ውስጥ ባለች በፈረስ ከተማ ከተማ አካባቢ፡፡ ይህ አንድነት የድማማ ዲክላሬሽን ተብሎ ነው የሚታወቀው፡፡ # በጎንደር ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ/ም በሻለቃ ሃብቴ ወልዴ የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝና በሻለቃ ባዬ ቀናው የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎንደር ፣ የጎንደር ፋኖዎችን አንድ ለማድረግ መስማማታቸውንና የጋራ ኮሚቴዎችን ማቋቋማቸው ማሳወቃቸው ይታወቃል፡፡ ጥር 12 ቀን 2017 ደግሞ የተጀመረው ስራ ተጠናቆ፣ በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ በይፋ ሁለቱን እዞች ያዋሃደው የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ተመሰረተ፡፡ ሻለቃ ሃብቴ ወልዲ መሪ፣ ሻለቃ ባዬ ቀናው ምክትል መሪ፣ ኮማንደር ሳሙኤል ባለድል ወታደራዊ አዛዥ የሆኑበት፣ ከ95% በላይ የጎንደር ፋኖዎች ያቀፈ፣ ጎንደርን አንድ ያደረገ አደረጃጀት፡፡ ይህ አንድነት የእንቃሽ ዲክላሬሽን ይባላል፡፡ #በወሎ አራት አደረጃጀቶች ነበሩ፡፡ አንደኛ በሻለቃ ምሬ ወዳጆ የሚመራው ከግማሽ በላይ ወሎን የሚሽፈነው አስደረጃጀት ነበር፡፡ ሁለተኛ እነ ሻለቅ አድርሳ የሚመሩት ከወልዲያ እስከ ደሴ ባለው ቁልፍ መስመር የሚንቀሳቀሰው የልጅ እያሱ ኮ ያለበት አሰላለፍ ነበር፡፡ ሶስተኛው እነ ወግዲና ቦረና(ደብረሲና) ወረዳዎች አካባቢ የሚንቀሳቀሰው በነ ሻለቃ ሃብታሙ ደምሴ የሚመራው አሰላለፍ ነበር፡፡ አራተኛ ደግሞ በኮሎኔል ፋንታሁን የሚመራ፣ ቤተ አማራ ኮር የሚባለውን ያካተተ፣ በዋናነት በዳዉንት፣ ደላንታና በጉባ ላፍቶ በተወሰኑ ቀበሌዎች የሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች ያቀፈው አደረጃእጅት ነው፡፡ ከነዚህ አራት አደረጃጀቶች፣ በኮሎኔል ፋንታሁን ከሚመራው አደረጃጀት ውጭ ያሉት ሶስት፣ በአጠቃላይ 90% የወሎ ፋኖዎች ያቀፉት አደረጃጀቶች በአንድ ላይ ተሰባስበው፣ የአማራ ፋኖ በወሎ በኢተ አማራ በሚል ስል አንድ አደረጃጀት ጥር 14 ቀን 2017 ዓ/ም መስርተዋል፡፡ ከ90% የወሎ ፋኖዎች አንድ የሆኑበት ስምምነት፣ መርጦ ዲክላሬሽን የሚል ስምያሜ ተሰጥቶታል፡፡ በኮሎኔል ፋንታሁን ስር ያሉ ክፍለ ጦሮችና ብርጌድ ሻለቃዎችም የአማራ ፋኖ በወሎ ቤተ አማራ አደረጃጀትን መቀላቀል የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ለመሪያቸው ለኮሎኔል ፋንታሁን አክብሮት ስላላቸው፣ ኮሎኔሉ ራሱን አፋህዴ ብሎ ከሚጠራው ውጤት አልባና ከፋፋይ፣ ወሎን የከፋፈለ ቡድን ለይቶ እንዲወጣ፣ ከሚያከብሩት፣ ከሚወዱት፣ አባታችን ብለው ከሚጠሩት፣ የወሎ ፋኖዎች ልጆቹ ጋር እንዲቀላቀል ጥረቶች እየተደረጉ ስለሆነ፣ ትንሽ እንታገስ ከሚል ነው የቆዩት፡፡ የወሎን አንድነት ከኮሎኔል ፋንታሁን ጋር ሆነን ነው የምንቀላቀለው ከሚል እሳቤ፡፡ ሆኖም ግን ኮሎኔሉ አይኑን ካልከፈተና ግትር አቋሙን ይዞ ከቀጠለ ትግሉ የህልውና ትግል እንደመሆኑ፣ የቤተ አማር ኮር ፋኖዎችም የግለሰ ክብር ዘበኛ ሳይሆን የህዝብ ፋኖ እንደመሆናቸው የራሳቸውን ውሳኔ መወሰናቸው አይቀሬ ነው፡፡ እንግዲህ ትልቁ ጥያቄ ሸዋስ የሚል ነው ????በሸዋም ችግሩ ያለው ጥቂት አመራሮች ጋር እንጂ በሁለቱም የሸዋ ዕዞች ውስጥ ያሉ የሸዋ ፋኖዎች አንድ እየሆኑ ነው፡፡ ውጊያዎችን በጋራ እያደረጉ ነው፡፡ እኛ የሸዋ ፋኖ እንጂ የ እስክንድር ነጋ ፋኖዎች አይደለንም ብለው የአፋህዴ የተባለው ቡድን እንደማይቀበሉ እየገለጹ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ አሁን አፋህዴ ከአገዛዙ ጋር ድርድር ማድረጉ ከተሰማ በኋላ የሸዋ ፋኖዎች ቁጣቸውን እየገለጹ ነው፡፡ ህዝቡም "አዋረዱን" እያለ ነው፡፡ ስለዚህ የ እዝ መሪዎች ምንም ምርጫ አይኖራቸውም ህዝብ ከማክበር፣ አንድ መሆን የሚፈልገውን ሰራዊታቸውን ከማዳመጥና የሸዋ ፋኖዎችን አንድነት እውን ከማድረግ ውጭ፡፡ ስለዚህ የአንዲት የሸወአ መንደር ስም ተጠቅሶ የዚህ ዲክላሬሽን የሚል መግለጫ በቅርቡ እንሰማለን ብዬ ነው የምጠብቀው፡፡ ሸዋ በጠቅላይ ግዛት ደረጃ አንድ ከሆነ በኋላ፣ ወለጋ ያሉትን ጨምሮ፣ አንድ ሁሉን ያካተተ፣ ሁሉን አሸናፊ ባደረገ መልኩ፣ በግለሰብ ተክለ ሰውነት ላይ ያልተገነባ፣ የአማራ ፋኖ የጋራ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራር ይኖራል፡፡ እንዳልኩት እየተጠበቀ ያለው ሸዋ ነው፡፡
GIRMA KASSA tweet media
AM
3
5
28
2.6K
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝና ውይይት/ድርድር የተባለው ነገር #ግርማካሳ በሻለቃ መከታው ማሞ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ፋኖዎችም መሪዎች ስራ ላይ ነው ያሉት፡፡ ዕዙ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ የሸዋ ፋኖዎችን አንድ ማድረግ አንገብጋቢና ትልቁ አጀንዳው እንደሆነ በመግለጫ ማሳወቁ ይታወቃል፡፡ አገዛዙ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ፋኖዎች በሚቆጣጠሯቸው ቀጠና ከፍተኛ ኃይል፣ አየር ወሎዶች ጨምሮ አስገብቶ ውጊያ ከፍቶ ስለነበረ፣ ከባድ ትንቅንቅ ተደረጎ አገዛዙ በሽንፈት የተመለሰበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ፋኖዎች፣ መሪዎችንም ጨምሮ በአሁኑ ወቅት ከአገዛዙ ጋር እየተፋለሙ ናቸው፡፡ ቁጭ ብለው ከነ ወርቅነህ ገበየሁ ጋር የሚነጋገሩበት ጊዜውም የላቸውም፣ ህሊናቸውንም የሸጡ አይደሉም፡፡ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ፋኖዎችም መሪዎቻቸውም፣ ውይይት፣ ድርድር ለሚባለው ነገር ጊዜም የላቸውም፡፡ አያውቁትምም፡፡ በእስክንድር ነጋ የሚመራው ራሱን አፋህዴ ብሎ የሚጠራውን ቡድን አደረኩ ያለውን ነገር አስመልክቶ፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ የለበትም፣ የእዙ የስራ አስፈጻሚ አልተነጋገረበትም፣ እውቅና አይሰጠውም፡፡ እኛን አይመለከትም" እያሉ እንደሆነ ነው የደረሰኝ መረጃ የሚጠቁመው፡፡ ይህን ስል በዕዙ ውስጥ ያሉ፣ ከዕዙ ፍቃድና ማንዴት ውጭ ከአፋህዴ ጋር እስክስታ የሚሉ የሉም ማለቴ አይደለም፡፡ ግን ዕዙ እንደ ዕዝ በአሁኑ ጊዜ ስራዎቹ ሁለት አንቸው፣ አንደኛው በሸዋ አገዛዙና ታጣቂዎቹን መሰባበር፣ ሁለተኛ የሸዋ ፋኖ አንነትን ማረጋገጥ፡፡
AM
0
0
3
226
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
የአፋህዴ መሪዎች፣ ህዝብንና ፋኖን ይቅርታ ይጠየቁ #ግርማካሳ ራሱን አፋህድ ብሎ የሚጠራውና በእስክንድር ነጋ የሚመራው ድርጅት፣ ከአራት አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ፣ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ፣ በድብቅና በሚስጥር ዳዎንት ወረዳ መገናኘታቸው ይታወቃል፡፡ ሆኖም ይህ በሚስጥር የተደረገ ንግግር ህዝብ ስላወቀው፣ "እነ እስክንድር ከአገዛዙ ጋር እየተደራደሩ ነው" በሚል ውስጥ ውስጡን ከፍተኛ ተቃውሞ ስለቀሰቀሰ፣ እስክንድር ነጋ የአፋህዴ መሪ በኢትዮ360፣ ረ/ፕ ጌታ አስራደ በአንከር ሜዲያና በኢትዮ ፎከስ ሜዲያ ላይ ቀርበው ፣ "ድርድር አላደረኝም፡፡ የተደረገው ውይይት ነው" በሚል ሰፊ ማስተባበያ ለመስጠት ሞክረዋል፡፡ "ድርድር ነው፣ ድርድር አይደለም" የሚል ውዝግብ ባለበት ሁኔታ፣ የቀድሞ የአሶሲየትድ ፕሬስ ዘጋቢ የነበረው፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ በመሰረት ሜዲያ ላይ " ከመንግስት ጋር ለመደራደር የተዘጋጀው የፋኖ ክንፍ ንግግሩ በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ እንዲሆን ጠየቀ ፡፡ ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ አልያም በአሜሪካ እንዲደረግ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል" ሲል አፋህድ ከአገዛዙ ጋር የድርድር ሂደት መጀመሩን ነው ያስታወቀው፡፡ የጋዜጠኛ ኤሊያስ ዘገባ ከአፋህድ መሪ፣ አቶ እስክንድር ነጋ ከፍተኛ ቅሬታንና ተቃውሞን ነው ያስተናገደው፡፡ ኤሊያስ ያቀረበው ዘገባ ውሸት እንደሆነ፣ መረጃዉን ያገኘው ከአገዛዝ ደህንነት እንደሆነ፣ አስፈላጊ ከሆነም የውጭ ድርጅቶችን ራሳቸውን መጠየቅ ይቻላል፣ ከአገዛዙ ጋር አልተደራደርንም" ረጅ ጊዜ ወስዶ በቲክቶክ ገለጻቸውን ሰጥቷል፡፡ በዚህ ሁኔታ ድርድር ተደረገ፣ ድርድር አልተደረገም የሚለው ክርክር እንደቀእለ፣ ዋዜማ ተጭዕማሪ ዘገባ ይዛ ወጥታለች፡፡ "በመንግስትና በተወሰኑ የፋኖ ታጣቂ ቡድኖች መካከል የተደረገው የመጀመሪያው የድርድር ማመቻቸት ሙከራ የተሳካ እንደነበረ በጉዳዩ የተሳተፉ የዲፕሎማቲክ ምንጭ ለዋዜማ ተናግረዋል።ስለውይይቱ ዝርዝር ይዘትና አንዳንድ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ መረጃዎችን መናገር እንደማይፈልጉ የገለፁት የዲፕሎማቲክ ምንጫችን ከፋኖ ታጣቂዎች አንድ አንጃ ከወከላቸው አባላት ጋር ውይይት ተደርጓል" ስትል ዋዜማ የተደረገው ድርድር መሆኑን ዘገባለች፡፡ በነገራችን ላይ ድርድር በሉት ውይይት፣ ሂደቱ በመርህ ደረጃ ችግር የለውም፡፡ ግን ለምን "ድርድር" መባሉ በዚህ መልኩ አስፈራ የሚለውን ጥያቄ ስናነሳ፣ ድርድርን ከመጥላት የተነሳ ሳይሆን፣ ከዘረኛው አገዛዝ ጋር የሚደረግ ድርድር ተዓማኒነት የሌለው፣ አገዛዙ ለጊዜ መግዣ የሚጠቀምበት ፣ የአገዛዙ ድራማ የሆነ ሂደት በመሆኑ ነው፡፡ አገዛዙ ችግሮች በውይይትና በድርድር ለመፍታት ፍላጎት ቢኖረው ኖሮ፣ የእስክንድር ነጋ ቡድን በዳዎንት ቁጭ ብለው ውይይት በሉት ድርድር በሚያደርገበት ጊዜ፣ በሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች የድሮን ጥቃቶችን እየፈጸመ ዜጎችን አይጨፈጭፍም ነበር፡፡ ቢያንስ ጊዚያዊ የተኩስ አቁም ያውጅ ነበር፡፡ ንጹሃን ዜጎችን በብዛት አይረሽንም ነበር፡፡ ያሰራቸውን በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩትን መፍታት ይጀመር ነበር፡፡ በሚቆጣጠራቸው ሜዲያዎችም የሚያሰራጫቸውን ፕሮፖጋንዳዎች ያለዝብ ነበር፡፡ አገዛዙ በአንድ በኩል ግፍና ሰቆቃ እየፈጸመ፣ በሌላ በኩል የሰላም ካዉንስል፣ የምክክር ኮሚሽን እያለ፣ እነ ወርቅነህ ገበየሁንም በአለም አቀፍ ድርጅት ስም እየላከ፣ ሰላም ወዳም መስሎ ለመታየት እያደረገ ያለው ድራማ ማንም የሚያወቀው ነው፡፡ እነ እስክንድር ነጋ ም ከማንም በላይ የአገዛዙን ባህሪ የሚያወቁ ናቸው፡፡ ስህተት ሰርተዋል፡፡ ስህተታቸውን አውቀው፣ ፋኖዎች፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው መስመራቸውን ማስተካከል ሲገባችው ፣ ስህተታቸው ለማስተባል ደፋ ቀና ማለታቸው አያዋጣቸውም፡፡ በዚህ ትልቅ የስህተት ሂደት የተሳተፉ ወገኖች አሉ፡፡ እስክንድር ነጋ እንኳን ይሰማል ብዬ አላስብም፡፡ ለምን ግትር ሰው ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ብዙ ምክረ ሃሳቦችን ሰጥተነው ሊሰማ ፍቃደኛ አይደለም፡፡ ከአንድ አመት በፊት እስክንድር ትልቅ ተቀባይነት ነበረው፡፡ አሁን ያ ተቀባይነቱ ተንኮታኩቷል፡፡ ያ እንዳይሆን ብዙ ተመክሯል፡፡ አልሰማም እንጂ፡፡ ስለዚህ እስክንድር ነጋ አሁንም ይሰማል ብዬ አላስብም፡፡ ምን አልባት ጥሩ የሰሩ መስሏቸው ይሆናል፡፡ ስህተቶች ይሰራሉ፡፡ ሆኖም ከስህተት መታረም ትልቅ ነገር ነው፡፡ እነ ረ/ፕ ጌታ አስራደ፣ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙኸባ ያሉ ወገኖች ግን ስህተቶቻቸውን ተቀብለው፣ ህዝብንና ፋኖዎችን ይቅርታ ጠይቀው፣ አፋህዴ የሚሉትን ቀልድ አቁመው፣ ራሳቸውን ከዚህ ሞተና ከበሰበሰ ድርጅት አውጥተው፣ ወደ ሚገባቸው ቦታ እንዲመለሱ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡
AM
0
0
2
169
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
አንዱ ከአፋህዴ ውይይት በሉት ድርድር ያደረገው ኢጋድ ነው፡፡ የኢጋድ መሪ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ ? የአዲስ አበባ ወጣቶች የጨፈጨፈው ወርቅነህ ገበየሁን፡፡ አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አድርጎት የነበረው ሰው፡፡ ሌላ በኢጋድ ውስጥ የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊ ነገር ነው መሰለኝ፣ ኦነጉ ሃይሉ ጎንፋ ነው፡፡ "አዎን ከነ ሃይሉ ጎንፋ ጋር፣ ከነ ወርቅነህ ገበየው ጋር ተነጋግረናል፡፡ ከብልጽግና ጋር ግን አልተነጋገርንም" ነው እንግዲህ እየተባልን ያለነው፡፡
GIRMA KASSA tweet media
AM
0
2
3
177
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
የወሎ ፋኖ የሃይል አሰላለፍ
GIRMA KASSA tweet media
AM
0
0
3
211
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
@dagmawi_belay ሻለቃ መከታውም ገብቶታል:: የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ከሌሎች የሸዋ ወንድሞቻቸው ጋር አንድ ለመሆንም መግለጫ አውጥተዋል::
AM
1
0
1
1.5K
Dagmawi M. Belay
Dagmawi M. Belay@dagmawi_belay·
ለመከታው ማሞ:- እስከንድር ነጋ ስራው የሆነ ቦታ ተቀምጦ በየ አቅጣጫው ስልክ እየደወለ ይህ ትግል የሚደናቀፍበትን ስራ ብቻ ነው የሚሰራው:: እስከዳር አይተኩስም አይዋጋም አያደራጅም ይህ ሰው ምንም እዚህ ግባ የሚባል ጠቃሚ አይሰራም:: ስራው 24/7 ሰሜን አሜሪካና አውሮፓ ካሉ እኩይ የስርዓቱ ግለሰቦች ጋር ተንኮል ሴራ ክፍፍል ንትርክ መፍጠር ብቻ ነው:: የፋኖን አደረጃጀት እኔ ካልመራሁ እበትነዋለሁ የሚል በጣም ግብዝ አቅሙን የማያቅ ሰው ነው:: ፋኖ የሚያክል ጀግና በገንዘብ እገዛና በስሬ አደርጋለሁ የሚል ታናሽ ሰው ነው:: አርበኛ ፋኖ መከታው ማሞ ለዚህ ሁሉ ስህተት በታሪክ ተጠያቂ እንደምትሆን እወቅ:: ጨዋው የሸዋ ህዝብ በጣም አዝኖብሀል:: ይህ ለነ አርበኛ መሳፍንት ክብር ያልሰጠ ስብስብ አንተን እንደ ማስቲካ አላምጦ ተጠቅሞብህ እንደሚጥልህ እወቅ:: በፍጥነት ይህን ትግሉን የሚያዳክም ስራ የሚሰራ ሾተላይን አጋልጠህ ስጥ:: ግልባጭ:- @eskinder_nega
Dagmawi M. Belay tweet media
AM
55
45
126
18.3K
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
የጎንደርና የሸዋ ፋኖዎች የአንድነት ጉዞ! የአማራ ህዝባዊ አንድነት ድርጅት ጉዳይ ? #wamera #ethiopiannews #ግርማካሳ
AM
0
0
2
97
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
እስክንድር ነጋ ሆይ፣ እነ ዶር አምሳሉ መሰሎች ሳይሆን ፋኖዎች ይበልጡብሃል #ግርማካሳ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የሚል ከአምስት ወር በፊት መቋቋሙ የሚታወቅ ነው፡፡ የዚህን ድርጅት ስያሜና መተዳደሪያ ደንብ ያጸደቁት፣ ሁሉም የአማራ ፋኖ እዞች፣ በሙሉ ስምምነት ነበር፡፡ ሆኖም መጨረሻ ላይ የቁንጅና ውድድር ይመስል፣ አመራሩን በሙሉ ስምምነት ማድረግ ሲገባቸው ፣ በምርጫ ብለው ነገሮችን አበላሹ፡፡ እስክንድር ነጋ አምስት ለአራት ተመርጫለሁ አለ፡፡ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙኸባ የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ምክትል ነበሩ በወቅቱ ፣ ኮሎኔል ታደሰ እሸቴ የአማራ ፋኖ በጎንደር ምክትል መሪ ነበሩ፣ ሻለቃ ሃብቴ ወልዴ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዋና መሪና ሻለቃ መከታው ማሞ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ መሪ፣ የድርጅቱ መሪ እስክንድር እንዲሆን ድምጽ ይሰጣሉ፡፡ አራቱ፡፡ እስክንድር የራሱን ድምጽ ሰጥቶ አምስት ሰጥቶ ነው እንግዲህ አምስት ለአራት ተመረጥኩ አለ፡፡ ለእስክንድር ድምጽ የሰጡት የእዝ መሪዎች ያንን ውሳኔ ሲወስኑ፣ በራሳቸው ፍቃድ እንጂ በስራቸው የነበሩ የክፍለ ጦር አዛዦችን አናግረው አልነበረም፡፡ ከዚህም የተነሳ፣ የኮሎኔል ታደሰ እሸቴ ውሳኔ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና መሪ ሻለቃ ባዬና የስራ አስፈጻሜው ወዲያው ነበር የሻሩት፡፡ ኮሎኔል ፋንታሁንም በስራቸው የነበሩ ክፍለ ጦሮች ግማሾቹ በተቃውሞ ከርሳቸው ተለይተዋል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ እነ ሻለቃ መከታውና ሻለቃ ሃብቴ ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ ነው የወደቁት፡፡ በአጭሩ አነጋገር የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ተዝለፍልፎ ሊሞት ትንሽ ነው የቀረው፡፡ የድርጅቱ መሪ ነን የሚሉት፣ እስክንደር ነጋና ጓዶቹ፣ ቆም ብለው በማሰብ፣ በምርጫ የሆነው ነገር እንደገና ተሰርዞ፣ አሁን ያለው አመራር ተበትኖ፣ ሌሎች የፋኖ እዝ አመራሮች እንደገና እንዲመለሱ ተድርጎ፣ ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ ፣ ትግሉን ወደፊት የሚያሻግር አመራር መፈጠር ነው ያለባቸው፡፡ ሆኖም ግን በውጭ ያሉ አንዳንድ ወገኖች የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት በዳያስፖራ የድርጅቱ ተጠሪ እንድንሆን ወክሎናል እያሉ ነው፡፡ ኮሚኮች ናቸው፡፡ ዶ/ር አምሳሉ አስናቀ የሚባል ሰው የድርጅቱ የአለማቀፉ ኮሚቴ አስተባባሪ እንደሆነ ነው የነገሩን፡፡ በነገራችን ላይ ማንም የማንም አስተባባሪ የመሆን መብት አለው፡፡ ሆኖም ግን አሁንም የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት አመራሮችን ደግሜ እመክራለሁ፡፡ አስጠነቅቃለሁ፡፡ ሜዳ ላይ በፋኖዎች ዘንድም ሆነ በህዝቡ ዘንድ ያላችሁ ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ብቻ ሳይሆን፣ እንደው በናንተ ላይ ያለው ተቃውሞና ንዴት በ እጅጉ እየጨመረ ነው እላቸዋለሁ፡፡ በተለይም እስክንድር ነጋ በቁም ነገር እንደ ቀድሞ ወንድምህ እመክርሃለሁ፡፡ ልብ ግዛ፡፡ እነ ሻለቃ መሳፍንት እንኳን አሁን ያሉትን እስከማለት ከደረሱ ነገሩ ምን ያህል የከፋ እንደሆነ እንዴት ማሰብ ያቅትሃል ???? የጎጃም ፋኖዎች ላንተ ሲሉ ሕይወታቸውን ገብረዋል፡፡ እንደዚያ እንዳልወደዱህ ፣ በኋላ ስለተቃወሙህ ከጎጃም ጥለህ ለመሄድ ተገደድክ፡፡ ሸዋ ገባህ፡፡ ሸዋም ተመሳሳይ ሁኔታ እያጋጠመህ ነው፡፡ ለረጅም ጊዜ ከነበርክበት ቦታ ከይፋት ጥለህ ሄደሃል፡፡ በዚያ ያሉ የሸዋ ፋኖዎች ስለተቃወሙህ፡፡ ወሎ በአንተ ስም የነበረውን ክፍለ ጦር ያንተን ስም ሰርዘው በሌላ ተክተውታል፡፡ ትንሽ የቀረው ቦታ ጎንደር ነበር ሲባል ደግሞ፣ ጠንካራ ያንተ ወዳጆችና ደጋፊዎች እነ ሻለቃ መሳፍንትም በአደባባይ እየነቀፉህ ነው፡፡ እስቲ ልጠይቅህ ማን ቀረህ ? ውጭ ያሉ ወዳጆችህ እነ ዶር አምሳሉ፣ ወንድም ሙሉጌታ አያሌው ያሉት ????? የላይ ላይና የማስመሰል ሳይሆን የተግባር ትሁት ሁነህ፣ ካስቀየምካቸውና ካስቀየሙህ ጋር ይቀር ተባብለህ፣ ስህተቶችን አርመህ፣ ብዙዎቻችን የምንሰጥህን ምክር ብትሰማና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ሌሎችን አቅፍ፣ የቡድን አመራር ዘርግቶ፣ አንድ እንዲሆን ብትሰራ፣ ቢያንስ እንደበፊቱም ባይሆን በትንሹ ተቀባይነትህ መመለስ ትችላለህ፡፡ የተቃወሙህም ይቅር ሊሉህ ይችላሉ፡፡ በነገራችን ላይ እስክንድር የቡድን አመራርን ተቀብሎ፣ እኔ መሪ ነኝ ከሚል ሁላችንም መሪ ነን ወደሚል ቢመጣ፣ መሪ መሆኑ ይቀጥላል፡፡ ብቸኛ መሪ ሳይሆን ከቡድን አመራሮች አንዱ፡፡ አይ ካለ ግን ብቸኛ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መሪ ሆኖ የሚቀጥለው ለሳምንታት ቢወዘ ለጥቂት ወራት ነው፡፡ ለምን የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት፣ የአመራር ለውጥ ካላመጣ አሁን ተዝለፍልፏል፣ ነገ መሞቱ፣ ተነገወዲያ ወደ መቃብር መግባቱ ስለማይቀር፡፡
AM
4
2
8
445
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
It is long overdue for Fano leaders to stop their nonsenses and form a unified leadership. We need FANO unified command NOWWWW!!!!
GIRMA KASSA tweet media
English
0
0
4
91
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
ከ5 ወር በፊት የተቋቋመው የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የተመሰረተበትን ዓላማ አላሳካም:: ድርጅቱ ከጎጃም ፋኖዎች 0% : ከወሎ 20% ድጋፍ ነው ያለው:: በጎንደር ከ80% ወደ 20% በሸዋ ከ50% ወደ 20% ድጋፉ ወርዷል:: አብቅቶልታል ማለት ይቻላል::
AM
0
1
2
75
GIRMA KASSA
GIRMA KASSA@wameraGK·
This is Girma Kassa. I was not a frequent X user. I have been mostly using the Facebook platform. Unfortunately, Facebook has become a platform that limits and hugely control free speech. Therefore, I will start using X more frequently.
English
2
1
4
80