Sabitlenmiş Tweet

ጥር 1፣ 2026 በውጪ ሐገር ባለው የኦሮሞ ነፃነት ግምባር - ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (የኦነግ-ኦነሰ) 45ኛ ዓመት የኦነሰ ቀን በሚከበርበት ወቅት የኦነግ-ኦነሰ ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት ጃል መሮ ድሪባ፣ ከፍተኛ አዛዦችና 5 የዞን ጦር መሪዎችም ሲገኙ፤ የኔትወርክ ችግር የገጠማቸው ጃል ገመቹ አቦዬ (ምክትል የጦር አዛዥ) እና የሰሜን ኦሮሚያ ጦር መሪ ጃል ቀሬንሶ እንዲሁም የመሃከለኛው ምዕራብ ጦር መሪ ጃል አብዲ Dhሁጋ ፋሺስት አብይ በአካባቢው ባለው ሕዝባችን ላይ የድሮን ጥቃት እያደረሰ በመሆኑ አልተገኙም።
በየኦነግ-ኦነሠ የውጪ አደረጃጀት ኃላፊ የሆኑት እና የኦነግ-ኦነሰ ጠቅላይ አዛዥ አማካሪ የሆኑት #ጃል_ጅሬኛ_ጉደታ ላይ አንዳንድ ከእውነታ የራቁ ክሶችና አሉባልታዎችን የሚያጸዳ እጥር ምጥን ያለ የተከበሩት የኦነግ-ኦነሰ ጠቅላይ አዛዥ #ጃል_መሮ_ድሪባ እንዲህ ብለው ገልጸውታል......."በጃል ጂሬኛ ላይ ተቃውሞ እየተካሄደ እንደሆነ እናያለን ምንም አታገኙም። ድርጅታችንንም ይመራል። ጃል ጅሬኛን ያስቀመጥነው እኛ ነን። ዋጋ ከፍሎበታል። ኃላፊነቱ ቤተሰቡን በትኖበታል። ሐገሩን ይወዳል። ኦሮሞን ይወዳል። ስርቆትንና እውሸትን ይጠላል። ለዚህ ነው አብረን የቀረነው።
በጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ግምባር - የኦሮሞ ነፃነት ከትግል ሜዳ የተሰጠውን ትዕዛዝ ተቀብሎ ነው የሚሰራው። እኔ ነኝ የማዘው። ትዕዛዜን ይቀበላል። ገደል ግባ እንኳን ብለው ለትግላችን ትርፍ አለው ከተባለ ገደል ግባ እንኳ ብለው 'እሺ' ነው የሚለው። ድጋሚ እንኳን አይጠይቅም። ለዚህም ነው የተሰጠው ሃላፊነቶች ላይ የሚሰራው። ያጣውን ደግሞ እኔና እሱ እናውቃለን። የሚውቁም ያውቃሉ። የራሱን የተሻለ ኑሮ መኖር አላቃተውም። ይህንን አያይዘው ነው የወከሉት። ኦሮሞ ነው የወከለው። ታጋዮቹ ናቸው የወከሉት። እሱን ጠልታችሁ ትግሉን መውደድ አትችሉም። እኔን ጠልታችሁ ኦነሰን መውደድ አትችሉም። እኛ አንድ ነን። አንድ ቤተተብ ነን ማለት ነው።” - በማለት አብራርተዋል #ጃል_መሮ_ድሪባ
AM














