abush
1.8K posts

abush retweetledi

@NatnaelMekonne7 የወያኔ ባለስልጣን ልጆች በአሜሪካ እና አውሮፖ ሲኖሩ የደሀው የትግራይ ልጆች ወደ ጦርነት ይማገዳሉ !!! No more TPLF
AM
abush retweetledi

የግንቦት 20ን ወይም የካቲትን እያወደሱ በየቀኑ በማኅበራዊ ሚዲያ ድምፃቸውን የሚያሰሙ ሰዎች፣ ዛሬ ህወሓት በትግራይ ወጣቶች ላይ የግዳጅ ጦርነት ምልመላ ላይ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ እየሆኑ ነው:: ፖለቲካዊ አቋም ሊለያይ ይችላል፣ ነገር ግን የወጣቶች ሕይወት ከማንኛውም ፖለቲካ በላይ ነው።
ለራሳችን የምንፈልገውን ፍትሕና ሰብዓዊነት ለሌሎችም ማሰብ አለብን። አንድ ወጣት በግድ በምታዩት መልኩ እየተገረፈ ወይም መብቱ እየተጣሰ ለግዳጅ ሲታፈስ ይህ የሚያሳስበን ጉዳይ መሆን አለበት፤ የተጎጂው ማንነት ወይም የፖለቲካ አቋሙ ሳይሆን ሰው መሆኑ ብቻ በቂ ምክንያት ነው።
የሰው ልጆች ለእርስ በእርስ ጦርነት በግድ ሲታፈስ ወይም መብታቸው ሲጣስ ዝም ማለት መፍትሔ አይደለም። ዛሬ የሚያስፈልገን የጦርነት ከበሮ ሳይሆን የሰላም፣ የፍትሕ እና የወጣቶች ሕይወት ጥበቃ ድምፅ ነው። መልክቴ ለግንቦት 20 እና ለየካቲት ከበሮ ደላቂዎች ይድረስ!
AM
abush retweetledi

የቻይንኛ ቋንቋ በኢትዮጵያ ሥርዐተ-ትምህርት ውስጥ ለማካተት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት @ProfKindeya ከአምባሳደር ቺን ሃይ(በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር) ጋር በዛሬው ዕለት ስምምነቱ መፈራረማቸው ጥሩ ዜና ነው ለተማሪዎች።
ለመላው ተማሪዎች ጥሩ ዕድል የሚሰጥ ቋንቋው ከዓለማቀፋዊነቱ አንጻር በቀላሉ በትምህርት ሲስተሙ ላይ እንዲገባ ማድረግ ትልቅ ውሳኔ ሊባል የሚችል ነው።

AM

@martinplaut That’s why we Ethiopian vote to our beloved prime minister ABIY AHMED!!
English

FO Talks: Prime Minister Abiy Ahmed Looks to Secure a Landslide Win in Ethiopia’s Election.
In this episode of FO Talks, Rohan Khattar Singh and Martin Plaut discuss Ethiopia’s election, which delivered a predictable Prosperity Party victory
fairobserver.com/politics/fo-ta…
English
abush retweetledi

የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም!
ለኢትዮጵያ ጦርነት አያስፈልጋትም። በተለይ ደግሞ ለትግራይ ህዝብ ጦርነት የሚባል ነገር አማራጭ ሆኖ መቅረብ የለበትም። ነገር ግን ሻቢያም ሆነ የሻቢያ ቅጥረኛው የህውሃት አንጃ ኢትዮጵያን በአፈሙዝ እሞክራለሁ ካለ ጦርነቱ እንዳለፈው ግዜ በድሮንና በተለመደው የውጊያ መሳሪያ ብቻ ይሆናል ብሎ የሚያስብ ካለ እጅግ ሞኝ ነው።
ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ልክ ቆማለች። የኢትዮጵያ ሰራዊትም ሊመጣ ለሚችለው ተገማች ፈተና ብቻ ሳይሆን ከፈተናው በኋላ ለሚመጣ ተግዳሮት ሁሉ ስራውን ጥንቅቅ አድርጎ ጨርሷል። ጦርነትን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ ማስቆም አይቻልም። "ሰላም ከፈለግክ ለጦርነት ተዘጋጅ" እንደሚባለው ከየትኛውም አቅጣጫ ሊሰነዘር ለሚችል ጥቃት ኢትዮጵያ ተዘጋጅታለች። የኢትዮጵያን አቅም ባረጀና ባፈጀ ካልኩሌተር በተሰራ ኋላቀር ስሌትና ጭንቅላት መከላከል የሚችል ሃይል እንደሌለ ግን አስረግጬ ለመናገር እፈልጋለሁ።
ጦርነት አውዳሚ ነው። ጦርነት ቀፋፊ ነው! ጦርነት አደገኛ ነው። ጦርነትን መጀመር ቀላል ነው። አቅደህ ጦርነትን እንደምትጀምረው ግን አቅደህ ከጦርነት እሳት መውጣት እጅግ አስቸጋሪ ነው።
ስለሆነም ተገንጣዩ የህውሃት አንጃና ጀሌዎቹ ከዚህ እብደታቸው ተመልሰው በጠረቤዛ ዙሪያ ብቻ ችግራቸውን እንዲፈቱ አበክረን እንመክራለን! የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም!

AM
abush retweetledi
abush retweetledi
abush retweetledi

“እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል” ገና ብዙ ነገር እንሰማለን! የግንቦት 20 አክባሪዎችና ለየካቲት ከበሮ መቺዎች ጨፋሪዎች ይህን ጉዳችሁን ስሙልኝ!
የጄኔራሎቹ ወንጀል በዘረፋ ብቻ የተወሰነ አይደለም። እንታገላለን ብለው ወደ በረሃ የወጡ የትግራይ ሴቶችን ህይወት አበላሽተዋል። በበሽታ ለክፈዋቸዋል በክለዋቸዋል። ወደ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ አካባቢ ጎራ ብለህ ከነበረ እነዛን ስፍር ቁጥር ያልነበራቸው ነብሰጡር ሴቶችን አይተሃቸዋል ? እነኛ ሴቶች በረሃ እያሉ በጄኔራሎቹ የፀነሱ (የተደፈሩ) ናቸው
የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባል የነበሩት አቶ ነጋ አሰፋ
AM

“የተዘረፈው የሀገር ሀብት ለጥቂቶች መበልጸጊያ ሆኗል”-የቀድሞው የህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ነጋ አሰፋ
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ወቅት በአማራ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች የተፈጸመው መጠነ-ሰፊ የንብረትና የገንዘብ ዘረፋ፣ የትግራይን ህዝብ ካዝና ሳይሆን የጥቂት ወታደራዊ መኮንኖችንና ባለስልጣናትን ኪስ ያደለበ እንደነበር ተጋለጠ።
ይህንን ይፋ ያደረጉት የቀድሞው የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ነጋ አሰፋ ናቸው “ከኮር በላይ ነን” በሚል የትዕቢትና የልዩነት አስተሳሰብ በትግራይ ውስጥ የቀሩት አካላት፣ በዋናነት በወርቅና በሌሎች ውድ ማዕድናት ዝርፊያ ላይ የተሰማሩ ናቸው።
ከጦርነቱ ጀርባ የነበረው የዝርፊያ እውነታ የህወሓት ታጣቂዎች እስከ ሰሜን ሸዋ ድረስ ዘልቀው በገቡበት ወቅት በርካታ ከባድ ማሽነሪዎች፣ የህዝብና የግል ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ከባንኮች የተዘረፉ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገንዘቦች ወዴት እንደደረሱ አቶ ነጋ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
“ይህ የተዘረፈው በርካታ ማሽነሪ ወደ ትግራይ ካዝናና ኢኮኖሚ አልገባም። ያ ሁላ መኪና እና ባንክ ተዘርፎ የት ነው የገባው ካልን፣ እያንዳንዱ [ግለሰብ] ሀብታም ሆነበት ነው” ያሉት አቶ ነጋ አሰፋ፤ ጉዳዩ በጥልቅ ተጠንቶና ኦዲት ተደርጎ በዝርፊያው የተሳተፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጀነራሎችና ኮሎኔሎች ስም ዝርዝር በምስጢር መውጣቱንም አመራሩ ጠቁመዋል።
ይህ የዘራፊዎች ስም ዝርዝር በአሁኑ ወቅት በደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) እና በአቶ ጌታቸው ረዳ እጅ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል።
የሰምረት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ነጋ አሰፋ፣ የህወሓት ታጣቂዎች በወሎ፣ በሸዋና በሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች ላይ ያደረሱትን ዘግናኝ የኢኮኖሚና የማህበራዊ መዋቅር ውድመት በዝርዝር አስታውሰዋል።
ይሁን እንጂ፣ ይህንን ሁሉ አውዳሚ ጥፋት በጎረቤት ህዝብ ላይ የፈጸሙት የህወሓት የፖለቲካ ልሂቃን፣ ዛሬም ድረስ በፈጸሙት ጥፋት ከመጸጸት ይልቅ ራሳቸውን እንደ ‘ብቸኛ ተበዳይ’ አድርገው የመሳል የተለመደ ስነ-ልቦናዊ ድራማ ውስጥ መሸሸጋቸውን አቶ ነጋ በቁጭት ገልጸዋል።
ይህ የአቶ ነጋ ይፋዊ ምስክርነት፣ ከጦርነቱ ማግስት ጀርባ ያለውን የሀብት ማጋበስ ፉክክርና በጥፋቱ በቀጥታ ተጠቃሚ የሆኑትን የነባር መኮንኖችን እውነተኛ ገጽታ ፍንትው አድርጎ ያሳየ ክስተት ሆኗል።
AM
