Unique🌼💚💛❤️🌼
2.4K posts

Unique🌼💚💛❤️🌼
@UniqueMoveon
💪 Real Power Comes by Empowering Others! 💪💚💛❤️💪አማራነት ይለምልም💪ዘረኛ ሲልህ ዘር አጥፊ በለው💪 #AmharaEmpowerment









4️⃣ WEEK FOUR BEYOND AWARENESS Focus: Final week centers one question: what actually ensures the safety, security, and survival of the Amhara people? We moves beyond moral appeals and identifies concrete mechanisms to ensure the survival, safety & security of Amharas.

ሐዘንና እንባዬ የስብራት ሳይሆን የጀግና ነው! ከዚህ በፊት በፃፍኩት ከዚህ በሚረዝም ውዳሴ ምክንያት ፥ “በኢቶሪካ አልበም የተዘፈነላት ኢትዮጵያ ናት እኮ ለአማራው መታረጃው!” “አድናቆትህንም በመጠኑ አድርገው!” ሐዘናችንና ስብራታችንን የምንቸረው አለን። " የሚል ግሳፄ ደርሰኝ። 😟 . . . እኔ የቴዲን አልበም የተረዳሁት ከዚህ በተለየ መልኩ ነው። እንደውም በዚህ ጉልበትና ችሎታ ታጭቆ ፥ ለኔው ስንክሳር የቆመ እንደዚህ አልበም አይገኝም! ለዚህ አንዱ ማሳያዬ የአልበሙ ቁጥር 1 ፥ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክም ቁጥር አንዱ ሙዚቃ “ዳስ ጣል” ነው። ምጡቁ የቴዲ ስራው “ዳስ ጣል” ፣ ስለ ሐገር ታላቅነት በደስታ አብረው እንዲዘምሩት የተቀመረ ብሔራዊ መዝሙር አይደለም። ከብሔራዊ መዝሙር በላይ ግን የሚበጅ ፋይዳን የተጠቀጠቀ ፤ ከጠራ እውነት ውስጥ የተጨለፈን ሐገራዊ ማቅን በዜማ የሚያሸበሽብ ዘመን ተሻጋሪ መዝሙር ግን ነው! 50 ዓመታት በሞላው የጥላቻ ስብከት ነጋሪት ሲጎሰምበት ለኖረ፣ ጥላቻ አካል አበጅቶ ማንነቴን የአገር ጠላት አድርጎ ስሎ ሲገድለኝና ሲያስገድለኝ 27 አመታትን በተሳደድኩባት አገር ፣ በተለይ ደግሞ የጥላቻን ማዕበል አካልቦ ዘርማንዘሬን ለማጥፋት የቻለውን ሁሉ ሙጣጭ ጉልበት አሰባስቦ ላለፉት 8 ዓመታት የጭካኔን ጥግ ፥ የግፍ ግፍ አንገፍግፍ ለተገፋብኝ ለኔ ፥ አገር ሊያቆም የተሰዋ አያት ያለኝ እኔ ፤ በኢትዮጵያ አንድነት አውድ ውስጥ የተዜመ ሙዚቃ ሰምቶ ቀና አፀፋ መስጠት ይቅርና ማሰብ ራሱ ፣ ጋብ ለማይለው ለገዳዬን ጥይት ፥ ጀርባዬ ይኸውልህ አልም በለኝ እንደማለት ነው። ነገር ግን በዚህ ስራ ቴዲ አፍሮ ስለፖለቲካዊ ድንበር ወይም አካባቢ አላዜመም። ያዜመው ስለመንፈሳዊ ቤቴ ነው። ያዜመው ስለ እውነት መልክዓምድር ነው። የእውነትን ጣራና ግድግዳዋን ነው በ”ዳስ ጣል” የሳለው። በ”ዳስ ጣል” አያቴ አገር በማቅናቱ ፤ ለነብሱ ሳይሰስት በመሰዋቱ ፤ “ታሪካዊ ጠላት” የሚል የቂጣ ስም ተለጥፎበት፥ ዘርማንዘሬ ለታረደብኝ፤ ይህ ዜማ መስታወት ሆኖ ፤ “ስቃይህ ይታየኛል” ይለኛል። የሞትኩ ፥ የታረድኩ ፥ የተሳደድኩ እኔን ብቻ ሳይሆን ገዳዬን አሳዳጄን በደም ከነጨቀየው እጁ ወለል አድርጎ ያሳየዋል። ስለዚህ ዳስ ጣል የአገርን የውርደት ማቅ ሲያሳይ የኔንም ፍዳ አሳየንጂ አልሸሸገውም። የገዛ ወገኔ የነፈገኝን የግፍ እልቂትና ውርደት፣ የሰው ልብ ውስጥ እየገባ “ዳስ ጣሉ” እያለ በሐቅ ይሞግትልኛል እንጂ ሽንገላ አልሰበከኝም። “አክሱምና ላሊበላን ፣ባንድ አለት አጽንቶ፤ አልራመድ አለ፣ አገር ተለያይቶ፤” . . . ሲል ለየትኛው ገድል እውቅና ሰጥቶ አድንቆ አመስግኖ? በየትኛው ደግሞ ልቡ የተሰበረ ይመስልኃል? ይህ ሁለት መስመር ስንኝ ፣ “አማራ ታሪካዊ ጠላት” ተብሎ እንደ ህዝብ የተከሰሰበትን ቅጥፈት፤ በሁለት መስመር የሚያደባይ ባለሁለት አፍ የሐቅ ሰይፍ ነው። ዛሬ ላይ ዘበት የሆነው “የአገር አንድነት” የሚንቁት አላስፈላጊ ተረት ሳይሆን ፥ ተዓምር መሆኑን በአንድ ዓለት ምሳሌ ቴዲ የተቀኘበት ምጥቀቱ ነው። ስለዚህ እንኳን ስለ ኢትዮጵያ ተዜመ በሚል ገርነት ይቅርታ ልጠይቅና ልሸማቀቅ ይቅርና፣ ኢትዮጵያ በደምና አጥንት የተጋመድኳት ፤ ድል ነስቼ የምወርሳት፤ የመንፈስ ቤቴ መሆኗን የአለቱ ምሳሌ መልሶ ያስታውሰኛል። እንደውም በዚህ አለት ላይ የህልውና ትግሌን አፅንቼ ወደፊት እገሰግሳለሁ። “አንሳው” የሚለው ድምፅ ፣ ኢትዮጵያን እንመራለን ብለው ፥ ላለፉት 8 ዓመታት በአማራው ላይ የጭካኔን ጣሪያ ሳይታክታቸው ከሚሰቅሉት አውሬዎች መናገሻ እንደተሰማ ጥሪ ሳይሆን፤ አማራው አማራጭ አጥቶ ለህልውናው የገባበትን ትንቅንቅ በበረታ ቁርጠኝነት እንዲገፋበት አድርጎ የሚያስወነጭፍ በጎ ጉልበት አድርጌ ነው የማየው። “አንሳው” ያለውን ባንዲራም ቢሆን “ሰንደቄ” ፥ “ዘውዴ” ፥ “ጌጤ” ብዬ አክብሬ የያዝኩት እኔው ነኝ። ግጥም አድርጌ አነሳው። የእውነትም በመጨረሻም በድል ይህንን ሰንደቅ ማንሳት ፣ ከፍ ማድረግ፣ በጨቋኜ ላይ የሚያደርሰው ሞራላዊ ድቀት የላቀ፣ ድሌንም ጣፋጭ ያደርገዋል። ኢቶሪካ ስቃዬን የሚሸፍንብኝ ፣ ኢትዮጵያ ብሎ የመጣ ጭምብል ሳይሆን ፣ እንደ አማራ ለአገር ሉዓላዊነት ፥ ክብርና ፅናት አያት አባቶቼ የከፈሉትን ዋጋ ሳይክድ ሳይከሰኝ ያከበረልኝ፤ እንዲህ በከፋው በዛሬው ቀን ደግሞ፣ እንደ ህዝብ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አማራ ላይ የሚወርድብንን ግፍ ፣ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይልኝ ፤ እስከ ዛሬ የጮህኩትን ጩኸት ከፍ አድርጎ ለ90 ሚልዮን ጆሮና ዓይን ያደረሰልኝ፤ ለኔም መልሶ ስቃዬን ያሳየኝ መስታወቴ ነው። ስለዚህ አልበሙን ሰምቼ ያጋራሁት ሐዘንና እንባዬ የስብራት ሳይሆን የጀግና ነው! @teddyafromuzika @HOAAffairs @Hohe421











