DANIEL HAILU ENDALE

4.1K posts

DANIEL HAILU ENDALE banner
DANIEL HAILU ENDALE

DANIEL HAILU ENDALE

@danhailuend

CEO & Founder @DanEnergyEt, @DanGlobalPM, @EagletsFuture Empowering Life, Empowering Nations #Science, #Technology, #Development

Addis Abeba, ETH. Dubai, UAE Katılım Ekim 2018
473 Takip Edilen2.8K Takipçiler
Abdi 🇪🇹
Abdi 🇪🇹@Abdrezak1584333·
@danhailuend የአንተም መገለጫ ነው ትጉነት በርታ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ሀገርና ትውልድ ያመሰግኑኋል
AM
1
0
0
30
DANIEL HAILU ENDALE
DANIEL HAILU ENDALE@danhailuend·
ጋሽ መርከቡ ! እጅግ ዘመናዊ የሆኑትን የ JUKI የልብስ መስፊያ ማሽኖቾ Tokyo, Japan 🇯🇵 በሚገኘው የ JUKI Corporation ዋና መ/ቤት በመገኘት በመጎብኘት ላይ ነን። እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1938 ዓ.ም የተቋቋመው JUKI ከ185 ሀገራት በላይ ምርቱን ይሸጣል ያሰራጫል። በአለማችን ታዋቂ የልብስ አምራቾች ዋነኛ ደንበኞቹ ናቸው። H&M Uniqlo እና የመሳሰሉት ። ለጨርቅ ለቆዳ ለሴንቴቲክ ሌዘር እንዲሁ ወረቀት መሥፊያ የሚሆኑ Industrial Sewing ማሽነሪዎችን ያመርታል። የእነዚህ ማሽነሪዎች ፍጥነት እና ቅልጥፍና ለመናገር እና ለመግለፅ አዲስ ቃል መፈጠር ይኖርበታል። በደቂቃ 5500 ጊዜ ይሰፋሉ። እስኪ አስቡት ? ከሥራ ባልደረቦቼ እና ከጃፓናውያን ወዳጆቼ ጋር ጉብኝታችንን ቀጥለናል። JUKI ከተመሰረተ ጀምሮ ያመረታቸውን ማሽኖች በሚያሳይበት Show Room ከተደረደሩት የልብስ መሥፊያ ማሽኖች ከፊት ተርታ የተቀመጠችው ቡናማዋ የሥፌት ማሽን ቀልቤን ስባ ወደ ተወለድኩባት እና ወደ አደኩባት ሰፈሬ አዲስ አበባ ሳሪስ ከሩቅ ምስራቅዋ ቶኪዮ ያለ ትራንስፖርት በአፍታ ቅፅበት አደረሰችኝ። የጋሽ መርከቡ ሁለቱም እግሮች ከማሽኗ ፔዳል ላይ ሆነው እየተነቃነቁ ለአካባቢው ነዋሪ ለኖረ ለተቀደደ ለሚያጥር ለሚሰፋ ለሚቀ- ጠል እና ለሚጣፍ ልብስ መስፌያ የሚሆነውን የእሽክርክሪት ጉልበት በጉልበታቸው እያመነጩ አብዛኛውን ጊዜ እንዳጎነበሱ እየሰፋ ይውላሉ። አለፍ አለፍ እያሉ በእጃቸው ጨመቅ ጨመቅ የሚያደርጓት የዘይት ማጠጫ የማሽናቸውን እድሜ ማራዘም ብቻ ሳይሆን የተቆራረጡ የሚተራርፉ ብጥስጣሽ ጨርቆች አንድ አይነት የዘይት ሽታ እንዲኖራቸው በተለያየ መዓዛ እና ጠረን ከየቤቱ የሚመጣውን ጨርቅ ልክ አስገብታ ሁሉን እኩል ሁሉን ልክ ታደርጋለች። ጋሽ መርከቡ መኖሪያቸው ሳሪሳ አቦ ይሁን እንጂ ለሥራ የመረጡት ግን የእኛን ሰፈር ነው። ለዚህ ዋነኛ ምክንያታቸው የሚጣፍ የሚለጠፍ የሚስተካከል እና የሚያጥር ልብስ በብዛት ያለው እኛ ጋር እና እታችኛው ሰፈር መሆኑ ነው። ለማስረጃ እኔ እንኳን በቁጥር የማላስታውሳቸውን የፋዘርን ሱሪዎች አስጠብቤ አሳጥሬ የማሰራው አንዱ ደንበኛቸው መሆኔ ነው። ሥራቸውን የሚወዱ በሥራቸው ልጆቻቸውን የሚያሳድጉ ብርቱና ትጉ ሰው ጋሽ መርከቡ። ሥራ ስለለመደላቸው በቅናሽ ዋጋ ለአካባቢው ነዋሪ አገልግሎት ይስጡ እንጂ በመስሪያ ቦታ ሲቸገሩ እንደነበረ አስታውሳለሁ። እትዬ ጠጅቱ ከቀበሌ ተከራይተው የሚኖሩበት ቤት በረንዳ ውስጥ ውስጡን ያለ ውል ለ ጋሽ መርከቡ አከራይተው ሳለ ልብስ ለማሰፋት እየመጡ እዛው የሚቀመጡ ሰዎች በመብዛታቸው እትዬ ጠጅቱ ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ አስለቀቁዋቸው። ፍትሐዊ ዳኝነት ለማግኘት ወደ አለማቀፉ ፍርድ ቤት ከመሄድ ይልቅ መንገዱን ሻገር ብለው ከ ዲባባ አጥር ስር ሰማያዊ የUNHCR ላስቲክ ወጥረው የማያቋርጠውን የልብስ ጥገና እና እድሳት ስራቸውን ቀጠሉ። በዙም ሳይቆዩ የብሄረ-ፅጌ መንገድ መስፋት እና አስፋልት መሆንን ተከትሎ ጋሽ ዲባባ ቦታውን ለቢዝነስ ለማልማት ግንባታ በመጀመሩ ለቀው ትንሽ ዞር ብለው አክመል ሱቅ ደጃፍ ላይ ስራቸውን ቀጥለው ደንበኞቻቸውንም አስከትለው ሄዱ። ጋሽ መርከቡ ደምበኞች ሲመጡ ፈገግ ብለው ይቀበላሉ። ፀሀይ ላይ ከመዋል ይሁን በተፈጥሮ ያላወኩት ጠቆር ያለው ፊታቸው ተከፍተው ወይም ተደስተው እንደሆነ አይናገርም ። ሚስጥረኛ ነው ። ጠዋት ይጀምራሉ ከት/ቤት ስመለስም እዛው ናቸው ጉንበስ እንዳሉ። ብዙ አመት ወደ ሁዋላ ከወሰደኝ ትዝታ እና ትውስታ ተመለስኩ። አስጎብኛችን ቀጠለ “ እንደምታዩት JUKI ከዚህች ማሽን ተነስቶ እዚህኛው ደርሷል” አለና አዲሱን እና ፈጣኑን ማሽን ማስነሻውን ጫን በማለት አስነሳው ተርርርን አለ በደቂቃ 5500 ጊዜ የመርፌ ጫፉዋን እያንቀሳቀሰ ። የቆመ እንጂ የተንቀሳቀሰ አይመስልም። የጋሽ መርከቡ የእግር እንቅስቃሴ እና የሚፈጥረው ዙር ከላይ የሚቀነሰው የሚጠበው የሚሰ-ፋው የፋዘር ሱሪ አልቆ ተሰፍቶ እስክለብሰው ድረስ የምጓጓውን ያህል የጋሽ መርከቡ ልጆች የት ደርሰው ይሆን? ራሴን ጠየኩ ጋሽ መርከቡ !
DANIEL HAILU ENDALE tweet mediaDANIEL HAILU ENDALE tweet mediaDANIEL HAILU ENDALE tweet mediaDANIEL HAILU ENDALE tweet media
AM
2
5
34
2.6K
Abdi 🇪🇹
Abdi 🇪🇹@Abdrezak1584333·
@danhailuend በትዝታ የተሞላ እውነተኛ የሕይወት ታሪክ ስራን እንደ ህይወታቸው የወደዱ ጋሽ መርከቡ ትጉነት እርሳቸውን ሊገልፅ አይችልም ለችግሮች መፍትሔ ማምጣት እንጂ ለችግሮች እጅ መስጠት የእርሳቸው ምልክት አይደለም ትውልድ የሚያነሳሳ ታሪክ ነው 👏ይህ
AM
2
0
0
73
GIRUM ZEGEYE TESFAHUN
GIRUM ZEGEYE TESFAHUN@girum_zegeye·
እዮብ እንኳን ደስ አለህ።በርታ! ወንድማችን እዮብ በሀሳቡ መሀል አየኝ እና መለሰልኝ አለ። ''ማየት'' ማለት ማ:የት (ማን የት) የሚል ሀሳብን በመሀሉ ይዟል። ማነው የሚያየን፣እኛስ ለመታየት የት ነን? የሚያየንን ያብዛልን! thank you Dear Mr. @danhailuend
DANIEL HAILU ENDALE@danhailuend

ጥበበኛው ! እዮብ ጥበበ ኢትዮጵያ የብዙ ታታሪ እና ልባም ወጣቶች ሀገር ናት ። የሁላችንንም ሙሉ ድጋፍ እና ክትትል ካገኙ ህልማቸው ይሳካል ። እዮብ ትልቅ ቦታ ደርሳችሁ ማየትን እመኛለሁ ። እናንተም ይቅናችሁ 🙏🏽

AM
1
0
1
79
Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
Abiy Ahmed Ali 🇪🇹@AbiyAhmedAli·
Today in Hawassa, Sidama Region, we proudly inaugurate the Toyo Phase 2, Origin, and Lumintech solar factories, alongside the HZ Gas plant at Hawassa Industrial Park. Together, the solar facilities will generate 11.3 gigawatts of clean energy annually, while HZ Gas will supply 900 tons of oxygen, 40,000 tons of nitrogen, and 7 tons of hydrogen each year. These four projects have created numerous jobs, expanding opportunity and powering livelihoods. Their production capacity is immense, but so is Ethiopia’s potential! #EthiopiaDelivers
English
99
336
1K
30.1K
ሚክያስ ተስፋዬ ሙሉጌታ Mikyas T. Mulugeta 🇪🇹
I tackled one of the biggest challenges of my 24 years in aviation — and I passed all 13 EASA ATPL exams. Praise be to God. At 46, this was not a walk in the park. It felt more like a marathon through a maize field. Long days and nights of study. Setbacks. Second chances. Doubts. And many trips to the Hellenic Civil Aviation Authority in Athens. On April 24, 2026 — I crossed the finish line. Why pursue an EASA license after already holding ICAO and FAA ATPL? Because working with Airbus, under EASA jurisdiction, made it more than just “recommended” — it made it relevant. The journey covered all 13 theoretical subjects: Air Law | Aircraft General Knowledge | Instrumentation | Mass & Balance | Performance | Flight Planning | Human Performance | Meteorology | General Navigation | Radio Navigation | Operational Procedures | Principles of Flight | Communications But beyond the technical knowledge, this challenge demanded something deeper. It pushed me to rely on core pilot competencies: • Communication • Leadership & Teamwork • Workload Management • Decision Making • Situational Awareness This experience revealed a level of discipline, resilience, and focus I hadn’t fully tested before. If your path ever requires you to pursue an EASA license — even with ICAO or FAA qualifications — it’s worth it. You don’t just earn a certificate… You become a more complete pilot. If I can do it, you can too. #Aviation #EASA #ATPL #Airbus #PilotLife #NeverStopLearning #Resilience
ሚክያስ ተስፋዬ ሙሉጌታ Mikyas T. Mulugeta 🇪🇹 tweet media
English
28
3
119
5.8K
MesfinYilma
MesfinYilma@Nsksn346319·
your dedication to empowering the next generation is truly transformative. By creating opportunities for our talented youth, you aren't just building careers, you are building the future of Ethiopia. Thank you for being a visionary leader and a catalyst for change.🇪🇹 🇪🇹
DANIEL HAILU ENDALE@danhailuend

ጥበበኛው ! እዮብ ጥበበ ኢትዮጵያ የብዙ ታታሪ እና ልባም ወጣቶች ሀገር ናት ። የሁላችንንም ሙሉ ድጋፍ እና ክትትል ካገኙ ህልማቸው ይሳካል ። እዮብ ትልቅ ቦታ ደርሳችሁ ማየትን እመኛለሁ ። እናንተም ይቅናችሁ 🙏🏽

English
1
4
0
95
DANIEL HAILU ENDALE
DANIEL HAILU ENDALE@danhailuend·
ጥበበኛው ! እዮብ ጥበበ ኢትዮጵያ የብዙ ታታሪ እና ልባም ወጣቶች ሀገር ናት ። የሁላችንንም ሙሉ ድጋፍ እና ክትትል ካገኙ ህልማቸው ይሳካል ። እዮብ ትልቅ ቦታ ደርሳችሁ ማየትን እመኛለሁ ። እናንተም ይቅናችሁ 🙏🏽
AM
2
12
45
1.6K
Samuel Thomas 🇪🇹
Samuel Thomas 🇪🇹@SamuelthThomas·
@danhailuend Happy Birthday Dan!! Ethiopia 🇪🇹 is blessed to have you! You are a true role model, and entrepreneur. Your strength, leadership, and dedication continue to inspire so many. Wishing you a year filled with success, health, and even greater impact!
English
1
0
2
55
DANIEL HAILU ENDALE
DANIEL HAILU ENDALE@danhailuend·
ምዕራፍ 48 The Colors of my Life በደራሲው ዘላለማዊ እቅድ የተፃፈው የህይወቴ ምዕራፍ ዛሬ 48 ኛው ላይ ደርሷል ተመስገን ። 🙏🏽 በየእለቱ እየተረኩት የምኖረውን የዚህን ድርሰት ገፆች ብዛት ስፋት እና ጥልቀት እንዲሁም የቀለም ድምቀት እና ስሜት በምን ያህል መጠን ለአንባቢዎች ለአድማጮች እና ለተመልካቾች እንደደረሰ እንደታየ እንደተሰማ እና እንደጠቀመ ባላውቅም በደራሲው አፃፃፍ ላይ ተንተርሼ ሳደምቅ ሳፈዝ ሳሰምር ሳወርድ እና ሳወጣ ስዘራና ስተክል ይኸው ዛሬ 48 አመት ሞላኝ። በስንት ምዕራፎች ፅፎ እንደሚጨርሰኝ ወይም እንደጨረሰኝ ልጠይቀው ፈለኩ እና መጨረሻ ወደሌለው እና ዳርቻው ወደ ማያልቀው ሰማይ ቀና ብዬ ደራሲውን “ጋሼ ስንት ነው?” ስለው “እሱ እንኳን ሚስጥር ነው” አለኝ ምድርን ለማረስረስ ከሰማይ ቀስ እያለ በሚያወርደው ዝናብ መካከል ፍንትው ብላ በማለዳ በወጣችው ፀሐይ ዛሬን እያደመቀ እና እያሞቀ ። ተመስገን አልኩና ወደ ነገ በሚወስደኝ የጊዜ አቅጣጫ በኩል መንገዴን አቀናሁ። ለዛሬ የተፃፈልኝን ገፅ ለማድመቅ እና ለመተረክ ተራመድኩ ። ደግሜ ተመስገን አልኩ። ተመስገን !
AM
2
8
25
780
Abdi 🇪🇹
Abdi 🇪🇹@Abdrezak1584333·
@danhailuend ምን ማለት እንዳለብኝ ባላውቅም Happy birthday to you ጀግናው ታታሪው ልበቀናው የብዙኋን ህይወቶች ብርሃን ከዚህም በላይ ....... ለህዝባችን ኑርለት 🤗🤗
AM
1
0
1
57
Narሜር💧🇪🇹
Narሜር💧🇪🇹@Afreeka00·
ተመስገን ፈጣሪ ጤና እና እድሜ ይጨምርልህ 🙏🏾
DANIEL HAILU ENDALE@danhailuend

ምዕራፍ 48 The Colors of my Life በደራሲው ዘላለማዊ እቅድ የተፃፈው የህይወቴ ምዕራፍ ዛሬ 48 ኛው ላይ ደርሷል ተመስገን ። 🙏🏽 በየእለቱ እየተረኩት የምኖረውን የዚህን ድርሰት ገፆች ብዛት ስፋት እና ጥልቀት እንዲሁም የቀለም ድምቀት እና ስሜት በምን ያህል መጠን ለአንባቢዎች ለአድማጮች እና ለተመልካቾች እንደደረሰ እንደታየ እንደተሰማ እና እንደጠቀመ ባላውቅም በደራሲው አፃፃፍ ላይ ተንተርሼ ሳደምቅ ሳፈዝ ሳሰምር ሳወርድ እና ሳወጣ ስዘራና ስተክል ይኸው ዛሬ 48 አመት ሞላኝ። በስንት ምዕራፎች ፅፎ እንደሚጨርሰኝ ወይም እንደጨረሰኝ ልጠይቀው ፈለኩ እና መጨረሻ ወደሌለው እና ዳርቻው ወደ ማያልቀው ሰማይ ቀና ብዬ ደራሲውን “ጋሼ ስንት ነው?” ስለው “እሱ እንኳን ሚስጥር ነው” አለኝ ምድርን ለማረስረስ ከሰማይ ቀስ እያለ በሚያወርደው ዝናብ መካከል ፍንትው ብላ በማለዳ በወጣችው ፀሐይ ዛሬን እያደመቀ እና እያሞቀ ። ተመስገን አልኩና ወደ ነገ በሚወስደኝ የጊዜ አቅጣጫ በኩል መንገዴን አቀናሁ። ለዛሬ የተፃፈልኝን ገፅ ለማድመቅ እና ለመተረክ ተራመድኩ ። ደግሜ ተመስገን አልኩ። ተመስገን !

AM
1
0
1
71
Pulp Faction
Pulp Faction@DanielsonKassa1·
Electrify everything is trending in Ethiopia ⚡️🇪🇹
Pulp Faction tweet mediaPulp Faction tweet mediaPulp Faction tweet mediaPulp Faction tweet media
English
21
42
261
18.9K
DANIEL HAILU ENDALE
DANIEL HAILU ENDALE@danhailuend·
@EmudyMoody አፋር ለጉብኝት በቅርቡ ሄጄ ነበር ። የሚደንቅ ሀገር የሚያስደምም ምድር የሚደነቅ ህዝብ ! አፋር ።
AM
0
1
1
31
EmNodi/Waaqa እምኖዲ/ዋቃ
🙏🏽🙏🏽🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Afar National Regional State President Office@AfarState

በአፋር ክልል በ62 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የአቅመ ደካማ ቤቶች ተመረቁ ​ወረር አዶብተሌ — በአፋር ክልል በዞን 1 እና በዞን 3 በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ለአቅመ ደካማ ዜጎች የተገነቡ 16 መኖሪያ ቤቶች ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች ተረከቡ። ​ለቤቶቹ ግንባታ በአጠቃላይ ከ62 ሚሊዮን 600 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ግንባታው የተከናወነው በዱብቲ፣ በአሚበራ (ወረር አዶብተሌ) እና በአዋሽ ከተሞች ነው። ​በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ሃጂ አወል አርባ እንደገለጹት፤ አቅመ ደካማ ዜጎችን መደገፍ በምድርም በሰማይም ከፍተኛ ዋጋ ያለው ተግባር ነው። ይህ በጎ አድራጎት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተጀመረው የ“ወገን ለወገን” መርሀ ግብር አካል መሆኑን በመጥቀስ፣ ሁሉም ዜጋ በዚሁ መንፈስ ሊረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል። ​የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በበኩላቸው፣ ፕሮጀክቱ “ከተረፈን ሳይሆን ካለን ለወገኖቻችን” በሚል መርህ የተከናወነ መሆኑንና ተደምሮ በመስራት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል። ​ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በክልሉ ከሚያከናውናቸው የውሃ፣ የሳኒቴሽንና የኢነርጂ አቅርቦት ስራዎች በተጨማሪ ማህበረሰቡን በዚህ መልኩ ማገዙ የሚደነቅ ተግባር መሆኑ በዕለቱ ተገልጿል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

ART
1
2
5
99
Abdi 🇪🇹
Abdi 🇪🇹@Abdrezak1584333·
Just two years PM @AbiyAhmedAli transformed Hawassa into something words can’t describe. Ethiopia 🇪🇹
English
10
36
145
4K
CNN International
Flying between African cities forces many travelers to transit outside the continent, through London, Paris or Dubai. But a $12.5 billion airport under construction in Ethiopia could help change that. cnn.it/4mLS4Bj
CNN International tweet media
English
111
927
2.7K
257.6K
Girma
Girma@GirmaTMS·
@danhailuend Good to see u back bec yr posts were lost in z air for weeks.
English
1
0
1
63
DANIEL HAILU ENDALE
DANIEL HAILU ENDALE@danhailuend·
ዙረት ! የልብ እስኪሞላ ያሰቡት እስኪደርስ ። በምስራቅ ቻይና የውቂያኖስ ዳርቻ ላይ ይገኛል Jiangsu province ። በታላቋ ሀገር ቻይና በልማት እና በእድገት ኢኮኖሚውን በቀዳሚነት ከሚዘውሩት እና ከሚያዘዋውሩት አንዱ ክፍለ ሀገር ነው Jiangsu እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር 19 March 2014 ከ 13 አመት በፊት መሆኑ ነው ከ Shanghai ለዋናው መዳረሻዬ Wuxi የያዝኩት ፈጣን ባቡር የክረምቱን ቀዝቃዛ አየር ሾጠጥ ባለው አፍንጫው እየሰነጠቀ ይምዘገዘጋል ። አቤት ፍጥነት ዥውውው ድርስ ቆም ውርድ ውርድ ግብት ግብት እንደገና ዥውውው ጭልጥ ከጊዜ ጋር ሽሚያ ከቀን ጋር ግብ ግብ። የተሳፋሪው ሰው ንቃት እና ቅልጥፍና ለጊዜ ያላቸውን ግንዛቤ ያሳያል። በመዳረሻው ባቡር ጣቢያ ሲጠባበቁኝ የነበሩት ቻይናውያን ወደ ከተማው እንብርት ወስደው ግሩም ምሳ ጋብዘው ጉዙ ወደ BAIFA ሆነ ። በ Wuxi ከተማ መሰረቱን የጣለው BAIFA POWER ታዋቂ የ ጀነሬተር አምራች ኩባንያ ነው። ጅማሬው ከትንሽ ይሁን እንጂ አሁን የደረሰበት ስፋት እና ከፍታ ያስደንቃል። ልክ እንደ አብዛኞቹ ግዙፍ የቻይና ኩባንያዎች። በተለያየ መጠን እና አቅም ተመርተው ተመርተው በረድፍ ተደርድረው የሚታዩት ጀነሬተሮችን ብዛት ላስተዋለ ሰው ለአብዛኛው የአለማችን ክፍል በቂ ሀይል ገና በበቂ እንዳልተዳረሰ ማሳያ ነው። የፋብሪካው ንፅህና የባለሙያዎቹ ትጋት እና ትብብር ያስገርማል። ቀናሁ ! ለህልሜ መሳካት ይጠቅሙኛል ያግዙኛል እማርባቸዋለሁ ብዬ ያመንኩባቸውን የኢነርጂ እና የቴክኖሎጂ ተቋማት በሚገኙበት የአለማችን ክፍል አቅሜ እና ሁኔታው በፈቀደልኝ መጠን እየዞርኩ እጎበኛለሁ ። ጠቃሚ ዙረት ! እንዳላችሁ ገመትኩ 😀 ከዙሩ አይቀር በልብ ለያዙት ህልም መዞር ።
DANIEL HAILU ENDALE tweet mediaDANIEL HAILU ENDALE tweet mediaDANIEL HAILU ENDALE tweet mediaDANIEL HAILU ENDALE tweet media
AM
1
6
31
2.6K