Mይሳው
77K posts

Mይሳው
@PPSlayer26
ዝንትአለም አማራ ድላችን መከበራችን በክንዳችን!!! የአውሬው መጨረሻ በፍጥነት እየተቃረበ ነው!!


Remember, the government cannot *discount* anything, nor provide “free” stuff. YOU are paying for that with your tax dollars. This is just communist money laundering and will collapse in spectacular fashion, decimating local businesses in the process.

All of these journalists in Gaza were killed by Israel


🚨 𝗢𝗙𝗙𝗜𝗖𝗜𝗔𝗟: World Cup final referee Slavko Vinčić has announced his retirement.








በምስራቅ አርሲ በአራት ዓመት 450 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ተባለ ለተከታታይ አምስት ዓመት ገደማ ማንነት ተኮር ጥቃቶች በተፈጸሙበት ምስራቅ አርሲ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የሚያረጋግጥ የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ዞን በዘጠኝ ወረዳዎች ከ2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ድረስ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ያካሄደውን የምርመራ ግኝት ይፋ አድርጓል፡፡ ኢሰመጉ ይፋ ባደረገበት 158ኛ ልዩ መግለጫው፣ በምስራቅ አርሲ የተለያዩ ወረዳዎች በተደጋጋሚ በተፈጸመው ጥቃት በአራት ዓመት ውስጥ ቢያንስ ከ450 በላይ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን አስታውቋል። መንግስታዊው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት በ37 ገጾች ቀንብቦ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ውስጥ ጥቃቶች ተፈጽመዋል፡፡ በታጣቂ አካላት ማንነትንና ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ በተፈጸሙ ጥቃቶች የሰው ህይወት ከማለፉ ባሻገር፣ በርካታ ዜጎች ለአካላዊ ጉዳት፣ ለእገታ እና ለአስገድዶ መሰወር ተዳርገዋል። ለዓመታት በቀጠለው ጥቃት ከ14,000 በላይ ሰዎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትና የግል ንብረቶች መዘረፋቸውንና መውደማቸውን አመልክቷል። ኢሰመጉ ባካሄደው የመስክ ምልከታና መረጃ የማሰባሰብ ስራ፣ በጥቃቶቹ ሳቢያ በየወረዳው የተመዘገበውን የሟቾች ቁጥር እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡፡ መርቲ ወረዳ፣ 117 ሰዎች፤ ሽርካ ወረዳ፣ 116 ሰዎች፤ ጀጁ ወረዳ፣ 101 ሰዎች፤ ሮቤ ወረዳ 47 ሰዎች፤ ጉና ወረዳ፣ 26 ሰዎች፤ ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፣ 20 ሰዎች፤ ሙኒሳ ወረዳ፣ 19 ሰዎች፤ አሰኮ ወረዳ፣ 5 ንጹሃን ዜጎች እና 4 የህዝብ ሚሊሻዎች ፤ አርሲ ሲሬ ወረዳ፣ 3 ሰዎች በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ሕይወታቸው አልፏል ተብሏል፡፡ ጉባኤው በምርመራ ውጤቱ የሟቾችን ስም ዝርዝር ከነምስላቸው አስደግፎም ነው በሪፖርቱ ይፋ ያደረገው፡፡ ከግድያው ጎን ለጎን በሽርካ፣ ሮቤ፣ ጀጁ፣ መርቲ እና ሙኒሳ ወረዳዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ የካሳ ገንዘብ ከፈለው ያስለቀቋቸው ቢኖሩም፤ የበርካቶች ያሉበት ሁኔታ እስካሁን ሳይታወቅ ቀርቷል። በጥቃቶቹ ወቅት በህጻናትና በአረጋውያን ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንም ሪፖርቱ ያመላክታል። የደህንነት ስጋቱ በዞኑ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፣ በጀጁ (6,216)፣ በሽርካ (3,746)፣ በአሰኮ (2,133)፣ በሮቤ (1,270)፣ በመርቲ (1,036)፣ በሙኒሳ (29) እና በጉና (21) ወረዳዎች በጠቅላላው ከ14 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን አስረድቷል። በተጨማሪም ዕድሜ ጠገብ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸውን፣ መዘረፋቸውንና በስጋት ምክንያት መዘጋታቸውን ይፋ አድርጓል። ኢሰመጉ ድርጊቶቹ በህገ-መንግስቱና በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተረጋገጡ መሰረታዊ መብቶችን የጣሱና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ባህሪያትን የሚያሳይ ነው ብሏል። የፌደራልና የክልል መንግስታት ለዜጎች ዘላቂ ጥበቃ እንዲያደርጉ፣ ጥሰት ፈጻሚዎችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ፣ ለተጎጂዎች ካሳ እንዲከፈልና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።









