
Tesfaye Neway
4.4K posts













ቀን፡ጥቅምት 10 2018 (October 20, 2025) የማንቂያ ሠነድ በአማራ ህዝብ ላይ ያንዣበበውን ወቅታዊ አስጊ አደጋ የሚያሳወቅ፣ ሊያመጣ የሚችለውን ጥፋት ለመቀነስ የሚያስችሉ ምልከታዎች ለመላው የአማራ ህዝብ፣ ለአማራ ፋኖ፣ ለሁሉም ፍትህ ወዳድ እንዲሁም ለሰብዓዊነት የቆሙ አካላት በሙሉ ___________________________ በመጀመሪያ በአራቱም አቅጣጫ ለአማራ ህዝብ ህልውና ስትሉ ታላቅ መስዕዋትነትን እየከፈላችሁ ላላችሁ ወንድም እህት ፋኖዎች፣ የአማራን ጭፍጨፋ ለማቆም፣ ለማሳወቅ እንዲሁም ፍትህ እንዲያገኝ ስትሰሩ የታገታችሁ፣ የታሰራችሁ፣ ያላግባብ ክስ ተጭኖባቹ እየተቃያችሁ ላላችሁ ወንድም እና እህቶቻችን፣ እንዲሁም በተመሳሳይ ሁኔታ ይህን ታላቅ የዘር ማጥፋት በመቃወማችሁ ስራችሁን፣ ንብረታችሁን ቤተሰባችሁን አጥታችሁ ተሰድዳችሁ አሁንም በሰው አገር ላይ ይህን ስቃይ ለማስቆም እየሰራችሁ ላላችሁ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተከላካዮች፣ ፖለቲከኞች፣ እንዲሁም በተለያየ ሁኔታ በመደራጀት፣ ወገንን በመርዳት ላይ ያላችሁ፣ በውጭም በአገር ውስጥም ላላችሁ ለአምሓራ ህዝብ ዘብ የቆማችሁ ወንድም እህቶች፣ እንዲሁም በመላው ኢትዮጲያ ይህ አገዛዝ እረፍት ነስቷችሁ፣ በተለያየ መንገዶች ውድቀቱን እያፋጠናችሁ ላላችሁ አካላት ባጠቃላይ፤ ሰላምታችን ይድረሳችሁ። የዚህ ሠነድ አላማ፤ ሁለገቡን የህልውና እንቅስቃሴ፤ ለመገምገም፤ ለመተቸት ወይም ለመምራት አይደለም። የዚህ ሠነድ አላማ፤ ሙሉ በሙሉ ከስሜት የተላቀቀ ጥሬ መረጃ ላይ ብቻ የተመሰረተ ወቅታዊ ትንተና በመስጠት፤ የስጋቶችን ቅደም ተከተል ለሁሉም ለአማራ ህዝብ ህልውና እና ፍትህ ከዚያም ባሻገር፣ ኢትዮጲያ ባጠቃላይ አሁን ከሆነችው በላይ ወደፍፁም ቀውስ እንዳትሸጋገር ለሚሰራ አካል ሁሉ እነዚህ ስጋቶች ከተወሰኑ የተመረጡ ስጋቶችን መቀነሻ ምልከታዎች ጋር በማድረግ ህዝብ ቀድሞ በመዘጋጀት እራሱን እንዲጠብቅ፣ የሚያስችል የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ለማስተላለፍ ነው። የሚቀጥሉት 2 ገፆች ላይ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ስጋት ያልነውን ጉዳይ ከተጓዳኝ፤ መፍትሄው ጋር አቅርበናል። ከተለያዩ ሰብዓዊ እና ዲጂታል ወቅታዊ የመረጃ ምንጮቻችን በመነሳት፣ እንዲሁም ከዚህ በፊት የተለያዩ የአማራ ዘር ጭፍጨፋን በመሰነድ እንዲሁም በመዘገብ የሚታወቁ ተቋማት ያወጧቸውን መረጃዎች በመቃኘት፣ እዚያም ላይ ተመስርቶ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ከዚህ በፊት የተደረጉ አሰቃቂ ጥቃቶችን ይዘት፣ ቅርጽ እንዲሁም ቅደም ተከተልን በተጓዳኝ በመተንተን የቅርብ ግዜ አስከፊ ስጋቶችን ዘርዝሮ ለህዝብ የሚያቀርብ አጭር የተጨመቀ ፅሁፍ ያቀረብን ሲሆን። እነዚህንም ስጋቶች ተክትሎ በምን አይነት እርምጃዎች ይህን የተገመተ ስጋት መቀነስ ወይም ማስቀረት ይችላል ለሚለው የኛን ምልከታ አሰቀምጠናል። አሁናዊ ስጋት፡ በአማራ ክልል ውስጥ ሊደረግ ስለሚችል ዘር ተኮር ጅምላ ጭፍጨፋ የጀርባ መረጃ አማራ ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ የመድረሱ ስጋት አዲስ አይደለም፡ ። ባለፉት 35 አመታት የአማራ ህዝብ ስርዓታዊ እና መንግስት መር በሆነ እቅድ የዘር ጭፍጨፋ ሲካሄድበት ቆይቷል። በተለይ አማራ ክልል ከሚባለው ቦታ ውጭ ያሉ አማራዎች በተለያየ ግዜ በተለያዩ ሽፋን ሰጪ ምክንያቶች አማሮች ሲጨፈጨፉ እና ሲፈናቀሉ ቆይተዋል። የአማራው ጭፍጨፋ በተለይም ‘ለውጥ’ የተባለው፤ የአሁኑ ገዥ ፖለቲካ ፓርቲ መደላደል ከተከሰተ በኋላ በአሰቃቂነቱም በድግግሞሹም እንደጨመረ የሚታወቅ ነው። ባለፉት 4 አመታት ደግሞ በተለያዩ አካላት ከማስጨፍጨፍ አልፎ በቀጥታ በአገር መከላከያ የሚመራ ይፋዊ ጦርነት አማራው ላይ ታውጆ በመላው በወቅታዊ የአስተዳደር ስሙ አማራ ክልል የሚባለው ክፍል ላይ ከፍተኛ ጦርነት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ሁሉ በአማራው ላይ በጦርነት ስም የሚደረገው የድሮን ጭፍጨፋ፣ የጅምላ ግድያ፣ የቤቶች ማቃጠል፣ የልጆችን ማፈን፣ የንብረት መውረስ እንዲሁም የተለያዩ ኢህጋዊ ድርጊቶች መፈጸም በህዝባችን ላይ የሚካሄድው አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ክስተት አካል መሆኑን አውቆ ህዝባችን እራሱን ለመክላከል ቆርጦ ተነስቶ የሚዋድቅበት ጉዳይ መሆኑ እንዳለ ሆኖ፤ አሁናዊ የስጋቱ አዲስ ተጨማሪ መልኮችንም በፍጥነት የማየትና ተገቢ የቅልበሳ ስራ ለመስራት ዝግጅት ማድረግ ግድ ይለናል። አማራ ላይ በግልጽ የተከፈተው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በወለጋ፣ በመተከል፣ በጉራ ፈርዳ በሰሜን ሸዋ እንዲሁም በተለያዩ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በንፁሃን ላይ ይደረጉ የነበሩ የተደራጁ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ጥቃቶች ላይ ይስተዋሉ የነበሩ አሰቃቂ የማሸበሪያ ድርጊቶች አሁን በጦርነቱ ከለላ እየተፈጸሙ መሆናቸው ስለድርጊቱ፤ ስለ አስፈጻሚው እቅድ እንዲሁም በመከላከያ ዩኒፎርም ተሸፍኖ ስለመጣው ፈጻሚ አካል ማንነት የሚነግሩን መረጃዎች አሉ። ይህ ማለት እንዲህ አይነት አሰቃቂ ድርጊቶች ባለፉት 2 አመታት በጦርነቱ ከለላነት አልተደረጉም ማለት አይደለም፤ ለምሳሌ በጎንደር በተደጋጋሚ ሁኔታ ሰዎችን ቤታቸው ውስጥ ከነህይወታቸው ማቃጠል፣ ጎጃም ላይ በጠራራ ፀሃይ ንፁሃንን ከተማ ውስጥ ከቤት እያወጡ መረሸን፣ ወሎ እና ሸዋ ላይ የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በመሆን ጦርነትን ማካሄድ፣ መዕመናንን ማሰቃየት፣ የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር በሴራ አማኞችን መግደል እንደምሳሌ ከየቀጠናው በብዛት የሃገር መከላከያ በሚል ሽፋን አማራ ክልል ውስጥ የሚያድርገው ወንጀሎች ሲሆኑ ከሚቀርቡት ዘገባዎች አንፃር በየቀጠናዎቹ እነዚህ የተዘረዘሩት ወንጀሎች እንደሚያመዝኑበት ቦታ ተቀመጠ እንጂ ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ እንዲሁም ሌሎች አያሌ በጦር ወንጀልነት እንዲሁም በዘር ማጥፋት ወንጀልነት የሚመዘገቡ ድርጊቶች በሁሉም ቀጠናዎች ሲፈጸሙ ከርመዋል። አዲስ መረጃ ከዚህ በፊት ሁለት አመት በፈጀው በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በተካሄደው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት፤ ወደጦርነቱ ማገባደጃ አካባቢ አገዛዙ፣ በኢትዮጲያ መከላከያ ስር የሰለጠኑ እና የተቀጠሩ ወታደሮችን ወደግዳጅ መላክ ወደማይችልበት ደረጃ ሲደርስ፤ የተለያዩ ክልሎች ልዩ ሃይላትን ወደርጦርነቱ ማስገባቱ ይታወሳል። ይህ የሚያሳየው፣ አገዛዙ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ግዢን ወጭ ለመሸፍን የሚችል የገንዘብ ምንጭ ከአገሪቱ በጀትም ይሁን በብድር ወይም በተለያዩ ፕሮጀክቶች ስም በልገሳ ከሚገኙ ምንጮት ማግኘት ቢችልም ጦርነት በጦር መሳሪያ እና ገንዘብ ብቻ የሚካሄድ ሳይሆን ሰብዓዊ ግባትም ስለሚያስፈልገው ይህ አገዛዝ ባለው አቅም ከ2 አመት በላይ የሚያስኬድ ከስልጠና እስከ ግዳጅ ያለውን ሰንሰለት የሚያሟላ ሰብአዊ አቅርቦት መቀጠል እንደማይችል ነው። እንደተገመተውም ይህ በአማራው ላይ የታወጀው ጦርነት 3ኛ አመቱን ሳይዝ ልዩ ሃይሎችን ወደጦርነቱ ማስገባት ጀምሯል። ከሰሜኑ ጦርነት ልዩ የሚያደርገው፣ በዚህኛው ዙር የኦሮሞ ክልል ልዩ ሃይል የመጀመሪያው በመከላከያ መለዮ ተሰላፊ መሆኑ ነው። በሰሜኑ ጦርነት የኦሮሞ ክልል ልዩ ሃይል ሌሎች ሃይሎች በተሳተፉበት መጠን እንዳልተሳተፈ እዚህ ጋር ማስገንዘብ እንፈልጋለን። ይህ ክስተት ለአማራ ህዝብ ከፍተኛ ስጋትን የሚፈጥርበት ምክንያት የኦሮሞ ልዩ ሃይል እንደ መከላከያ ወይም እንደሌሎች ክልሎች ልዩ ሃይሎች እንደመደበኛ ጦር ብቻ የሚንቀሳቀስ ሃይል ሳይሆን በወለጋ በተደረጉ ጥቃቶች እንደተገነዘብነው በመደበኛ ጦር ስልጠና እንደሚሰጠው መደበኛ ጠመንጃዎችን እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ የጦር መሳሪያዎችን ብቻ የሚጠቀም ሳይሆን (ይህ ማለት ለጨበጣ ወጊያ ጥቅም ላይ የሚውሉ ጠመንጃ ላይ የሚተከሉ ሳንጃዎችን ሳይጨምር) ከጨበጣ ውጊያ ውጭ ንፅሃንንም ይሆን በጦርነት ወቅት የተያዙ ታጋዮችን ከውትድርና ፕሮቶኮል ውጭ ሰውነትን በመዘልዘል፣ በመቆራረጥ፣ በማሰቃየት፣ የተለያዩ የአካላት ክፍሎችን ቆርጦ በማውጣት የተጎጂውን አካል ለህዝብ የሚታይ ቦታ በመተው የስነልቦና ሰብራት በመፍጠር ለማሸነፍ የሚደረግ አካሄድን ስለሚከተሉ ነው። ይህ አሰራር (Protocol or Modus Operandi)በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ያዋሉት ሲሆን፤ ለውጥ የተባለው ሽግሽግ ከመጣ በኋላ በቋሚነት ከኦነግ፣ መከላከያ ውስጥ ከተቀበሩ የኦነግ እና ኦሮሞ ብልፅግና እቅድ አስፈጻሚ አካላት፣ ከጋቸና ሲርና አደረጃጀቶች እንዲሁም ኦሮሞ ክልል ውስጥ ካሉ ሚሊሺያና የፖሊስ አባላት ጋር በቅንጅት ሲደረግ የነበረ ድርጊት ነው። ከላይ የተጠቀሱት አካላት ባንድም ይሁን በሌላ በኩል በነዚህ አይነት ጥቃቶች ይሳተፉ እንደነበር፤ ዩኒፎምና መለዮዋቸውን እንደለበሱ አብረው ጥቃቶችን ሲፈጽሙ የሚያሳይ የተንቀሳቃሽ ምስል እንዲሁም የተለያዩ የፎቶግራፍ፤ የምስክር እንዲሁም የድምጽ ማስረጃዎች አሉ። ማጠቃለያ ይህ አሁን በገፍ አማራ ክልል ላይ የገባው የኦሮሞ ልዩ ሃይል በአጭር ግዜ ውስጥ ለህዝባቸው ሲሉ የተሰዉት ባለም ዋሴና ትዕግስት ወዳጆ ላይ የፈጸመውን ጭካኔ በከፍተኛ ፍጥነት በሁሉም እግሩ በረገጠባቸው ቦታዎች ሁሉ በስፋት ሊፈጽመው እንደሚችል የሚያሳዩ ፍንጮት እየታዩ ነው። እነዚህ ጥቃቶች ሴቶች ላይ ማተኮራቸው፣ አገዳደላቸው ፍፁም ጭካኔ የተሞላበት መሆኑ፣ አልፎም ለመደበቅ ምንም ሙከራ ሳይደረግ ወደህዝቡ አካላቸውን ወርውረው መሄዳቸው፣ መቶ በመቶ ወለጋ ላይ የተደረጉትን ጥቃቶች ይዘት የሚያሟላ ነው። ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥቃቶች ላይ እንደተገንዘብነው፣ የነዚህ ጥቃት ዘመቻዎቻቸውን እንደነሱ መመዘኛ “ስኬታማ” የሚያስብለው ፍፁም ጭካኔውን አይቶ አማራው ነዋሪ ሸሽቶ ወደጫካ እንዲገባ ማድረጋቸው፣ ከመደናገጥ የተነሳ ተረጋግቶ ተደራጅቶ መመካከር እንዳይችል፣ የጋራ የመልሶ ማጥቃት እንዳያደርግ ልብ ሰልቦ ሊያጠቁት የመጡትን ህዝብ መልሶ የማጥቃትን፣ እንዲሁም ራስን የመከላከልን እድሉን ለመቀነስ የሚደረግ አስቃቂ ቲክቲክ ነው። ይህን በሚያደጉበት ወቅት ትልቁ ጠንካራ ጎን ይሆናችው የነበርው የተለያዩ በመንግስት ስም እና በ “ተቃዋሚ” ስም የተሰለፉ አካላት በጀርባ ተቀናጅተው መስራት መቻላቸው ነው። ይህም መከላከያ፣ የኦሮሞ ልዩ ሃይል፣ ጋቸና ሲርና፣ ሼኔ እንዲሁም የአካባቢ ሚሊሺያና ፖሊስ ተቀናጅቶ እንዲሰራ የሚደረግበት አካሄድ ነው። ይህን አይነት ሁኔታ ሊፈጥር የሚያስችል አስጊ ሁኔታ በወሎ ቤተአማራ እና ሸዋ ቀጠናዎች ውስጥ ቀድመው አዘጋጅተዋል። ይህም ‘ኦሮሚያ ልዩ ዞን’ በሚል አስተዳደራዊ ሽፋን ሰፊ የሆነ ቦታ ላይ የኦነግ/ኦነሠ፣ ሸኔ፣ ጋቸና ሲርና እንዲሁም የአስተዳደሩ ሚሊሺያን ጨምሮ የፖለቲካዊ እንዲሁም ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጡ እና ተወርዋሪ ሃይሎችን ሲያዘጋጁ ከርመዋል። ይህ ማለት ወለጋ የተደረገውን የአማራ ጭፍጨፋ ያመቻቸ የሚመስል የአስተዳደራዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ወታደራዊ አውድ በአማራ ክልል ውስጥ “ኦሮሚያ ልዩ ዞን” የሚል አስተዳደራዊ ከለላ በጦርነት አዋጅ በመከላከያ ዩኒፎርም ወደ አማራ ምድር ለገባው የኦሮሞ ልዩ ሃይል ሊፈጠር ችሏል። ስለዚህ፤ ወደ ‘አማራ ክልል’ የገቡት የተወሰኑ ወታደሮች ብቻ እንደሆነ ተደርጎ ከተወሰደ የስጋቱ በከፍተኛነት ሳይታሰብበት የከፋ ውድቀት ሊያደርስ ይችላል። ይህን የታቀደ ጭፍጨፋ፤ በአጭሩ ለመግታት፤ ስጋቱን ከስሩ መንቀል የሚችል ደፋር አካሄድ ያስፈልጋል። አስቸኳይ መፍትሔ በአጭር ግዜ ውስጥ የአፋብኃ ምስራቅና ደቡብ ቀጠና ውስጥ ያሉ እዞች እንዲሁም ሌሎች ከአፋብኃ ውጭ በተደራጀም መልኩ ይሁን በተናጠል የሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች መሪ ተሳታፊነት፤ በሁለቱ ቀጠናዎች ባሉ ነዋሪዎች ሙሉ ደጋፊነት ፤ እንዲሁም ባጠቃላይ በክልል ውስጥም ይሁን ከክልሉ ውጭ ባሉ እንዲሁም በውጭ አገር በሚገኙ ፍትህ ወዳድ አካላት የማያወላውል የጀርባ ደጋፊነት፤ ይህን በአስተዳደር ከለላ የተቀመጠ፤ ለጭፍጨፋ ዝግጁ የሆነ መዋቅርን ሙሉ በሙሉ ከሁለቱ ቀጠናዎች ውስጥ በማፈራረስ እና በሰላም ፈላጊና ከዚያው በአካባቢው ላይ በተወለዱ የአማራና ኦሮሞ ተወላጆች እንዲስተዳደር በማድረግ፤ ይህ ለአመታት፤ የአካባቢውን ነዋሪ ኦሮሞዎች ራሱ በመግፋት ለተለያዩ ቅጥር ቦታዎች እጩዎችን ከወለጋ፤ ጅማ እና አርሲ የአገዛዙን ካድሬዎች በማምጣት፤ አማራን ከውስጥ ለማስመታት ሲደራጅ የነበረን ፀረ አማራ አደረጃጀት በማፍረስ፤ ከላይ በስጋት 1 ስር የተተነተነውን አደጋ መቅረፍ እንደሚቻል ማሳወቅ እንወዳለን። ይህ አድረጃጀት መልክዓ ምድሩን ከተከተልን ወሎ/ቤተአማራን እና ሸዋን ታኮ የተቀመጠ ቢሆንም፤ ሰላዮችን እና ተዋጊዎችን በተለያየ ግዜ ተልዕኮ በመስጠት፤ በጎንደርና ጎጃም ቀጠናዎችም ሽብር ሲፈጥር እንደከረመ የሚታወቅ ነው። ስለሆነም ይህን የአደጋ ምንጭ ማፍረስ ባጠቃላይ በአማራ ክልል ውስጥ የታቀዱ የጅምላ ጥቃቶችን፤ የሰርጎ መግባት እቅዶችን፤ እንዲሁም የአገዛዙን የስለላና ሳቦታዥ አውታሮችን በመበጠስ አገዛዙን መሃል አገር በመሄድ ጨርሶ ለማፍረስ የሚደረገውን ትግል በከፍተኛ የሆነ ሁኔታ የሚያመቻች ይሆናል። በአማራው ውስጥ ሆን ተብሎ በሚላክ የተሳሳተ መረጃ እየተፈጠሩ ያሉ አለመግባባቶችም በሚታይ ሁኔታ እንዲቀንሱ ያደርጋል። አምሓራ ዘብ የሀሳብ ማዕከል ምንግዜም ዝግጁ













