TrueSeal
19.2K posts


ይሄ የቴሌግራም ቻናል በአንድ ወቅት የህዝብ ድምፅ እንዳልነበር አሁን በተቃራኒው የህዝብን ብሶት እየተከታተለ ማፈን ላይ ተጠምዷል፣ በዚህ ሳምንት ብቻ: - ከ130 በላይ ወጣቶች የቴዲ አፍሮን አዲስ ሙዚቃ ሰማችሁ ተብለው በግፍ ሲታፈሱ እንዲሁም ከአርቲስቱ ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ በጠራራ ፀሐይ ታስረው ሲወሰዱ አንድም ሳይዘግብ ከታች ያለውን የፖሊስ ማስተባበያ ይዞ ወጥቷል - ከቅጠል ተራ የሚነሱ እጅግ ከፍተኛ ድህነት ውስጥ ያሉ ዜጎች ተነስተው ዘመናዊ ቤቶች ሲገነቡ እነሱ የት ሊሄዱ ነው? ተብሎ ሲጠየቅ ዜናውን በዕለቱ ሳያቀርብ ቀርቶ በነጋታው የመስተዳድሩን መረጃ ብቻ ይዞ ወጥቷል። - ዛሬ ደግሞ ውል እና ማስረጃ አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ፣ አየር ጤና፣ ቦሌ ቡልቡላ እና ሰሚት ፍየል ቤት ያሉ ቅርንጫፎቹን እንደሚዘጋ ለሰራተኞቹ ማሳወቁን፣ እስከ ሐምሌ 1 መሉ በሙሉ ተዘግቶ በመሶብ አገልግሎት እንደሚተካ እና ሰራተኞቹ ምደባ ሳይካሄድላቸው ከነቤተሰቦቻችው ጭንቅ ላይ እንደሆኑ ለመሠረት ሚድያ ሲናገሩ "ቅርንጫፍ ቅነሳ ሊኖር ይችላል፣ ግን አይዘጋም" የሚል የተለመደ የመንግስት ቃል ብቻ ሰራተኞቹን ሳያነጋግር ይዞ ወጥቷል። ህዝብ በዚህ ወቅት ድምፅ የሚሆነው እንጂ የሚያፍነው ሚድያ የሚያስፈልገው አይመስለኝም፣ ተገደው ከሆነም ቢያንስ የሚጮኹትን ዜጎች ድምፅ ለማካተት መሞከር የሚድያ ስነ ምግባር ነው።





#ዜናመሠረት የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን አልበም መውጣትን ተከትሎ በፖሊስ በተያዙ ግለሰቦች ዙርያ የሚያጠነጥን ዘጋቢ ፊልም እየተሰራ መሆኑ ታወቀ በእስር ላይ የምትገኘው የአርቲስቱ ምክትል ማናጀር “የአርትስ ቲቪ መግለጫን ሳንከለከል እንደተከለከልን አድርገን የገለፅነው የሙዚቃ አልበሙ በሕዝብ ዘንድ ትኩረት እንዲያገኝ እና ማስታወቂያ ለመስራት ነው” ብላ ዶክመንታሪው ላይ እንድትናገር እየተጠየች እንዳለ መረጃ ደርሶናል የፕሪሚየም አባል ከሆኑ ሊንኩን ይከተሉ: meseretmedia.org/p/c50 በ30% ክፍያ የፕሪሚየም አባል ለመሆን ሊንኩን ይከተሉ: meseretmedia.substack.com/30pcoff

Press Statement The Centre for Human Rights is gravely concerned by reports of harassment and arrests linked to Ethiopian artist Teddy Afro following the release of his album Etorika. Artistic freedom must be protected. Read the full statement: chr.up.ac.za/press-statemen…





















